1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና የኤኮኖሚ ምጥቀት ትንበያ

ሐሙስ፣ መስከረም 3 2005

በኤኮኖሚ ፈጣን ግስጋሴ፤ ወደፊት ነብር የሚያሰኘውን የቅጽል ስም ቀጥሎ የሚያገኘው የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም መሆኑን፤ አንድ በበርሊን የሚገኝ የህዝብና ልማት ምርምር ተቋም አካሄድኩ ባለው የጥናት ውጤት በመመሥረት አስታወቀ። ተቋሙ፤ አፍሪቃ፤

https://p.dw.com/p/168Q8

ከህዝቧ ብዛት ጋር ኤኮኖሚዋን ለማዳበር በተፈጥሮ ሁኔታዎች የተማቻቹላት ናት ባይ ነው። ይኸው የሸማቾችን ፣ የገበያንና የትርፍን ጉዳይ የሚያጠናው ተቋም ስላካኼደው ጥናት፣ የዶቸ ቨለ ባልደረባ ፊሊፕ ሳ ን ድ ነ ር ያቀረበውን ዘገባ ፣ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው ሰብሰብ አድርጎ አቅርቦታል።

ተቋሙ ፤ 4 መለኪያዎችን መሠረት በማድረግ ፣ ባካሄደው ጥናት 50 የአፍሪቃ አገሮችን መዳሰሱን ያስታወቀ ሲሆን፤ ትኩረት የተደረገባቸው ነጥቦች፣ የኤኮኖሚ አንቀሳቃሽ «ሞተሮች»፤ የፖለቲካ ይዞታ፤ የህግ ፍትኅ ይዞታ፤ የህዝብ ብዛትና አጠቃላዩ የኑሮ ቅድመ ግዴታዎች ናቸው። ይህ ጥናት እንዲካሄድ ስለተደረገበት ምክንያት ራይነር ቪልድነር የተባሉት የተቋሙ ባልደረባ እንዲህ አብራርተዋል።

Entwicklungshilfe Afrika
ምስል picture-alliance/ZB

1,«ስለ አነዚህ አገሮች የነበረው መረጃ በአጅጉ ጥቂት ነው። አሁን በመጨረሻ ለማንሠራራትም ሆነ እመርታ ለማሳየት የተነሣሳው ክፍለ ዓለም አፍሪቃ ነው ። የዕድገት ግሥጋሴውን ፍጥነት ሲመለከቱት፤ቀጣዩ ነብር ወይም «ታይገር» የሚሰኘው አፍሪቃ ነው።»

ይህ የጥናት ውጤት ፤ ስለአፍሪቃ ዘርፈ ብዙ ችግር እየሰማና እያየ በኖረው ትውልድ ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ምስቅልቅል የሚታዩባቸው ታላላቅ ከተሞች፤ በሞት -ሽረት ላይ ሆነው ለህልውናቸው የሚፍጨረጨሩ ብዙ ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች ይዞታ ፣ አወንታዊው ገጽ አይታያቸውም። የበርሊኑ ተቋም፤ ለየት ሥዕል ነው የሚያቀርበው። የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ራይነር ክሊንግሆልትዝ እንደሚሉት፤ ለአንድ ሀገር ልማት፤ ወሳኙ፤ የህዝቡ አኀዝ ንረት ለውጥ ሲታይበት ነው።

2, «በማደግ ላይ በሚገኝ ህዝብ፤ ወላጆች የልጆቻቸውን ቁጥር ሲመጥኑ፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሥራ ዕድል የሚያገኘው ክፍል ይጠናከራል። የልጆች ቁጥር መጠን እንዲቀነስ ማድረጉ፣ የነፍስ ወከፍ ብሔራዊ ያልተጣራ ገቢ ከፍ ይላል። ሁኔታዎች ሲሳኩ፤ ዜጎች ሥራ የሚያገኙበት የዕድል በር ይከፈታል። ይህም ሲሆን የአፍሪቃ አገሮች፣ በጣም ጥሩ የዕድገት ፈር መቅደድ አይሳናቸውም።»

20 Jahre Frieden in Mosambik Sena-Eisenbahnlinie
ምስል Marta Barroso/DW

ይህ በተለይ ሞሪሸስን ደቡብ አፍሪቃንና አንዳንድ የሰሜን አፍሪቃን አገሮች የሚመለከት ነው። በዛ ያለ የኅብረሰብ ክፍል በሥራ መስክ ሲሠማራ ደግሞ ብዙ መሸመትም ሆነ ብዙ ዕቃ መግዛት ይችላል። እናም ፣ ክሊንግሆልትዝ እንደሚሉት፤ ጥረት በሚያደርጉት የአፍሪቃ አገሮች፣ መካከለኛ ገቢ ያለው የኅብረሰብ ክፍል እየተበራከተ መሄዱን ያስተውሏል። እርግጥ ፤ አቅማቸውን ፣ በጀርመን ሀገር ከሚገኙ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሰዎች ጋር የተስተካከሉ ይሆናሉ ማለት አይደለም።

Michael Monnerjahn የተባሉት ፤ ከጀርመን ኤኮኖሚ ጋር ፣ የተሣሠረው የአፍሪቃ ማኅበር የተሰኘው ድርጅት ባልደረባ ም ፣ አፍሪቃ በኤኮኒሚ መምጠቅ የሚስችል አቅም እንዳለው፤ ይህ ደግሞ ለጀርመን ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች አማላይ መሆኑን ነው የገለጹት። የሥነ ቴክኒክ ውጤቶችና ለደንበኞች የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ ዕድገት በማሳየት ላይ ለሚገኘው የአፍሪቃ ህዝብ ምንጊዜም ጠቃሚዎች ናቸው።

4,«በተለይ በባንክ ዘርፎች ወይም በመገናኛ አገልግሎት ዘርፎች ዐቢይ የዕድገት እመርታ ታይቷል። ይህ በእርግጥ ከ 15 ዓመት በፊት እንዲህ ይሆናል ተብሎ ጭራሽ የታ,ሰበ ሁኔታ አልነበረም። አዳዲስ የደንበኞች መገልገያ ዘዴዎች ተፋፋፍተዋል። ለምሳሌ ያህል በእጅ ስልክ የሚካሄደውን የባንክ አገልግሎት መጥቀስ ይቻላል። በዚህ ረገድ ፣ ኬንያ ፤ በዓለም ውስጥ የመሪነቱን ሥፍራ ይዛለች።»

20 Jahre Frieden in Mosambik Sena-Eisenbahnlinie
ምስል Marta Barroso/DW

የዕድገት ተስፋቸው ይበልጥ ብሩኅ መሆኑ የሚነገርላቸው አገሮች የበርሊኑ ተቋም እንደገለጸው፤ የባህር ጠረፍ ያላቸው 10 አፍሪቃውያት ሃገራት ናቸው። በደቡብ ፤የክፍለ ዓለሙ አካባቢ፤ ደቡብ አፍሪቃ፤ ናሚቢያ፤ በሰሜን ፤ ሞሮኮ፤ ቱኒሲያና ግብፅ፤ ከአነርሱም ጋር ፤ ሴኔጋል፤ ጋምቢያ ፣ ጋና፤ ጋቡን፤ እና ሞሪሸስ ይገኙበታል። በጥናቱ ላይ አስገራሚው ሁኔታ ዐቢይ የዕድገት ተስፋ ያላቸው ሁለት አገሮች፤ ኬንያና ናይጀሪያ አለመጠቀሳቸው ነው። ለዚህ የተሰጠው ምክንያት፤ ራይነር ክሊንግሆልትዝ እንዳሉት፤ በፖለቲካ ያለው አለመረጋጋትና ለጥሩ ኑሮ ቅድመ ሁኔታዎች መጥፎዎች መሆናቸው ነው።

Stau in Luanda Angola
ምስል DW

ኬንያ፤ ቁጥሩ በመናር ላይ ያለውን ህዝቧን በቂ ምግብና መድኀኒት በማቅረብ ችግሩን የምትወጣው አትመስልም። ናይጀሪያም እንዳለው ዘመን ሁሉ በነዳጅ ዘይት ሃብቷ አሁንም ተጠቃሚዎቹ ጥቂት የአስተዳደሩ አካላትና ተባባሪዎቻቸው ብቻ ናቸው።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ