1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና የዕድገቱ ዓይነት፤

ሰኞ፣ ነሐሴ 10 2002

20 ከመቶ የኤኮኖሚ ዕድገት ። ለአውሮፓውያን ይህ ህልም ብቻ ነው። አፍሪቃ ውስጥ ግን በተለይ ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በገፍ ትቸበችብ በነበረችው በአንጎላ ይህ ከጥቂት ዓመታት በፊት ህልም ሳይሆን ተጨባጭ ሀቅ እንደነበረ የሚካድ አይደለም ።

https://p.dw.com/p/OorD
የምጣኔ ሀብት ኮሚሽን ለአፍሪቃ፣የ ጽ/ቤቱ ህንጻ ፣ በ አዲስ አባባምስል picture-alliance/ dpa

በአጠቃላይ በአፍሪቃ ኤኮኖሚው ማደግ ከጀመረ ዓመታት አስቆጥሯል። ግን ይህ አዝማማሚያ አንድ ቀን መሪር ፍጻሜ እንዳይኖረው ማሥጋቱ አልቀረም። የአፍሪቃ ኤኮኖሚ በሰፊው የተመረኮዘው በጥሬ ዕቃ ሽያጭ ላይ ነው። ትኩረት የተደረገው ቶሎ ትርፍ በሚያስገኝ ነገር ላይ ነው። ለዚህ ድግሞ ስግብግብ ባለወረቶች አልታጡም። የዶቸ ቨለ ባልደረባ አድሪያን ክሪሽ የጻፈውን ዘገባ ፤ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ከንዑሳውያኑ ኩባንያዎች የሚመደበው ፣ ሆኖም ቀጣይነት ባለው ልማት ላይ በማትኮር የታወቀና ውጤታማ መሆኑ የተነገረለት አንድ የጀርመን የደን ልማት ድርጅት፤ ሃሪ አሰንባኸር የተባሉትን ሥራ አስኪያጅ መፈክር በማንገብ ፣ «በጎ ነገር ሠርቶ ትርፍ ማግኘት!» የሚል መርኅ ይከተላል። አሰንባኸር፤ ባለወረቶች፤ የአዳጊ አገሮችን ደን እንዲያለሙ ነው የሚወተውቱት። በ 20 ዓመታት ገደማ ውስጥ፤ ባለወረቶቹና ሠረታኞቻቸው ሊከስቡ እንደሚችሉም ነው አሰንባኸር የሚገልጹት። ለብዝኀ-ኅይወት ሚዛን ፣ከፊሉ ደን እንዲጠበቅ በማድረግና ቀሪውን በመጠቀም ፤ የሚበጅ ተግባር ማከናወን እንደሚቻል፤ አሰንባኸር፣ በረጅም ጊዜ አቅድ በፓናማና ቪየትናም ደን ማልማታቸውን ሲገልጹ፣ በተጠቀሱት አገሮች ያን ማድረግ የተቻለው፤ የተረጋጋ ሁኔታን የፀና ደንብ በመኖሩ ነው ብለዋል። ይህ የሆነው ሆኖ በየሀገራቱ የሚያጋጥም አይደለም።

«በአፍሪቃ ፕሮጀክቶችን እንድንዘረጋ ለምሳሌ ያህል ከካሜሩንና ኮንጎ ሐሳብ ቀርቦልን ነበር። ይሁንን ተቀዳሚ ሁኔታዎችን በመመርመር ማፈግፈጉን መረጥን። በተጠቀሱት አገሮች፤ የፖለቲካው ይዞታና የሥራ መመሪያ ደንቦች፣ ለመደበኛ ባለወረት፣ የሚዳሰስ የሚጨበጥ አይደለም ፤ የሚያስተማምንም አይደለም። »

የሃሪ አሰንባኸር ዛፎች ፤ ተተክለውና አድገውና ተቆርጠው አገልግሎት እስኪሰጡ ቢያንስ 20 ዓመት ስለሚወስድ በብዙ የአፍሪቃ አገሮች ይህ ዓይነቱ ፕሮጀክት ተቀባይነት የሚያገኝ አልሆነም። በጊኒ ባህረ-ሰላጤና በኒዠር ደለል፤ ነዳጅ ዘይት አካባቢውን በክሏል። በማዳካስካር ደን ክፉኛ ይመነጠራል የጀርመን የ Lebniz ዓለም አቀፋዊና አካባቢያዊ የምርምር ተቋም (GIGA)ፕሬዚዳንት ሮበርት ካፐል እንደሚሉት በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው።

«በምዕራብ አፍሪቃና በኮንጎ የደን መመንጠርን ስንመለከት ቀጣይነት ያለውን ልማት አያመላክትም እርግጥ ነው ወደ ውጭ ለገበያ በማቅረብ ገቢ ማስገባትና ገንዘብ እንዲዘዋወር ማድረግ ይቻላል። ግን ቀጣይነት ያለው ልማትን የሚጠቁም አይደለም። አፍሪቃ በኢንዱስትሪም ወደፊት የማትገፋ ከሆነ፤ ዕድገቲቱ ዘላቂነት አይኖረውም። አንድ ቀን ጥሬ ዕቃ ያልቅና ብርቱ ጥፋት ሊያጋጥም ይችላል። ትልቅ ድቀትም ሆነ ጥፋት ሊደርስ ይችላል የሚለውን ትንበያ በአፍሪቃ ማንም መስማት አይፈለግም። የአፍሪቃ ልማት ባንክ እንደገለጸው ዘንድሮ የአፍሪቃ የኤኮኖሚ ዕድገት 4,5 ከመቶ ይሆናል። በዚህ መጠን እንደሚቀጥልም፤ ምልክቶች ያሳያሉ። ይሁንና ዕድገቱ የተመረኮዘው፤ ጥሬ-ዕቃ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ብቻ ነው መለስተኛም ሆነ መደበኛ እንዱስትሪ ከስንት አንድ ነው ማግኘት የሚቻለው። ክፍለ-ዓለሙ፤ ነዳጅ ዘይትና ለከፍተኛ የሥነ-ቴክኒክ ጠቀሜታ የሚውለውን ማዕድን ኮልታን ይሸጣል። ጋናዊው ፊልም ሠሪና የፖለቲካ ተማሪ ደ ሮይ ክዌሲ አንድርው በድሀነት የሚኖር ዛሬን እንጂ ነገን አያስብም ይላል።

«ዛሬ ከሌለ፤ ነገም አይገኝም። የአሁኑ ትውልድ ለወደፊቱ አቅድ እንዲያወጣ ዛሬ ከሞላ ጎደል የተመቻቸ ኑሮ s እንዲኖረው ማብቃት ይኖርብናል። ቀጣይነት ያለው ልማት ሲባል ምናልባት ምዕራባውያኑ እንደሚያስቡት ዓይነት ላይሆን ይችላል። የበለጸጉት መንግሥታትም ቢሆኑ ቀጣይነት ያለውን ልማት እንዲቀጥል ለማድረግ የቻሉ አልሆኑም። »

በመሆኑም ሮበርት ካፐል ፣አፍሪቃ ፣ ቀጣይነት ስላለው ልማት ከምዕራቡ ስህተትም መማር ይችላል ባይ ናቸው። አፍሪቃ የራሱን የዕድገት ርእዮት መከተልና ለልማቱ አነቃቂ ኃይል መስጠት ይጠበቅበታል።

«የአፍሪቃ መንግሥታት ምናልባትም የአፍሪቃ ኩባንያዎች በተባለው ልማት ላይ ተጽእኖ የማሣረፍ ዕድል አላቸው። ጥቅጥቅ ያለውን ደን ከመመንጠር በፊት ቀጣይነት ስላለው ልማት ውል መፈራረም አለብን ሊሉ ይችላሉ። የተራቆተውንምድር መልሶ ደን ማልበስ ወይም ቀጣይ ልማትን ለማካሄድ መጣር ይኖርባቸዋል። ይህ ግንዛቤ የለም ማለት አይቻልም። አሁን 100 ሚልዮን ዩውሮ የሚያወጣ ምርት ለውጭ በማቅረብ ማግኘትና በኋላ የ 300 ወይም 400 ሚሊዮን ዩውሮ ኪሣራ ውስጥ መግባት ትርጉም የለሽ ነው። ይህ በፍጹም የሚያከራክር አይደለም።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ