1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃን ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በጀርመን ሀገር

ቅዳሜ፣ የካቲት 13 1996

አፍሪቃ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በጀርመን ሕዝብም ሆነ በፖለቲከኞቹ ዘንድ ያን ያህል ትኩረት ያላገኘ አህጉር ነበር ቢባል ስህተት አይደለም። ይሁንና፡ ይኸው ሁኔታ በወቅቱ ቀስ በቀስ በመቀየር ላይ ያለ መስሎዋል። የጀርመን መራሔ መንግሥት ጌርሃርት ሽረደር ባለፈው ጥር ወር አጋማሽ ላይ፡ እርሳቸው ለአህጉሩ ተስፋ ሰጪ ናቸው ያሉዋቸውን አራት አፍሪቃውያት ሀገራትን፡ ማለትም፡ ኢትዮጵያን ኬንያን፡ ደቡብ አፍሪቃን እና ጋናን ከዚሁ ጊዜ ቀደም ሲልም ጀርመናዊው ው

https://p.dw.com/p/E0l8

ጭ ጉዳይ ሚንስትር ዮሽካ ፊሸር ማሊን፡ ናሚቢያና ደቡብ አፍሪቃን ጎብኝተዋል። የፊታችን መጋቢት ወር ደግሞ የጀርመን ርዕሰ ብሔር ዩሐንስ ራው ወደ ታንዛንያና ናይጀሪያ ይጓዛሉ። የፌዴራዊት ጀርመን መንግሥት የፖለቲካ ማሠልጠኛ ማዕከል አሁን ባስቀመጠው ዓላማውም መሠረት፡ እአአ ከ 2004 እስከ 2006 ዓም ድረስ በመሥሪያ ቤቱ መርሐ ግብር ውስጥ ለአፍሪቃ ልዩ ትኩረት ለመስጠት ወስኖዋል። ማዕከሉ በተለያዩ የሙዚቃ ትርዒቶች፡ በኤግዚቢሽን፡ ወዘተ፡ አማካይነት ለጀርመናውያን ስለ አፍሪቃ የበለጠ መረጃ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል። በዚሁ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በሚዘልቀው መርሐ ግብሩ መሠረትም፡ ከጥቂት ሣምንታት በፊት በርሊን ውስጥ አፍሪቃን ማስተዋወቂያ ያለውን የመጀመሪያውን ዝግጅት አካሂዶ ነበር፤ በዝግጅቱ የተሳተፉት አፍሪቃውያን፡ እንዲሁም፡ ጀርመናውያን የወቅቱና የቀድሞ ባለሥልጣናት በሰፊው ተወያይተዋል።

ጀርመናውያን ስለ አፍሪቃ ከሞላ ጎደል አንዳችም መረጃ እንደሌላቸው ይነገራል። ለምሳሌ፡ የፌዴራዊት ጀርመን መንግሥት የፖለቲካ ማሠልጠኛ ማዕከል ፕሬዚደንት ቶማስ ክሩገር እንዳስታወቁት፡ ብዙ የጀርመን ተማሪዎች አፍሪቃን ከሀምሳ የሚበልጡ ሀገሮች እንደሚጠቃለሉበት አህጉር ሳይሆን ዋና ከተማዋ ጆሐንስበርግ የሆነች ጥቁር ሕዝብ የሚኖርባት እና ብዙ የዱር አራዊት የሚገኝባት አንዲት ነጠላ ሀገር አድርገው ይመለከታሉ። ይህ ገሀድ ሲታሰብ ታድያ ማዕከላቸው በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ትኩረቱን በአፍሪቃ ላይ ለማሳረፍ መወሰኑ ትክክለኛ ርምጃ ሆኖ ተቆጥሮዋል። ትኩረት ለአፍሪቃ የተሰኘው መርሐ ግብር በጀርመን ሀገር የተስፋፋውን አፍሪቃን እንደ አንድ ተስፋ የሌለው አካባቢ የመመልከቱ ገፅታ ልክ አለመሆኑን በማሳወቁ፡ የተሰረፀውን የተሳሳተ አመለካከት በመስበሩና የአህጉሩን ችግሮች ሳይደባብቁ በዚያ የሚታዩትን አወንታዊ ሂደቶች በማጉላቱ ረገድ ሰፊ ድርሻ የማበርከት ዓላማ ይዞ ተነሥቶዋል። አህጉሩን ለማያውቁት ለብዙዎቹ ጀርመናውያን አፍሪቃ የጦርነት የውዝግብ፡ ረሀብን የመሳሰለው የመቅሠፍት ተመሳሳይ መሆንዋን በበርሊኑ ዝግእጅት ተሳታፊ የነበሩት የቀድሞው የጀርመን ርዕሰ ብሔር ሪኻርት ፎን ቫይትሴከር በማስረዳት፡ ከአፍሪቃ ሥነ ፅሑፍ፡ ከሙዚቃዋና ከኪነትዋ ጋር በቀጥታ ግንኙነት በማድረግ አፍሪቃን በራሱ ጥረት የሚያውቅ ጀርመናዊ ስለ አህጉሩ በሚያገኘው መረጃ እጅግ እንደሚገረም ገልፀዋል። አፍሪቃ በተሐድሶ ለውጥና ባልተቋረጠው እንቅስቃሴ ላይ የምትገኝ አህጉር ናት። የጀርመን ፖለቲካና ኤኮኖሚም ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ለዚሁ አህጉር የበለጠውን ትኩረት ማሳረፍ ጀምሮዋል። የጀርመን መራሔ መንግሥት ጌርሃርት ሽረደር ወደ አፍሪቃ በተጓዙበት ወቅት አስከትለውት በሄዱት በግዙፉ የኤኮኖሚና የባለኢንዱስትሪ ተቋማት ተወካዮች ቡድን ውስጥ አንዱ የነበሩት የዳይምለር ክራይስለር ተጠሪ ማትያስ ክላይነርት ጀርመናውያን ባለተቋማት በአፍሪቃ የተነቃቃው የልማት ጥረት መልካሙን ውጤት እንደሚያስገኝ ማመናቸውን በማስረዳት፡ አፍሪቃውያን ለቀጣዩ ትውልድ የትምህርትና የሙያ ሥልጠና ለማቅረብ ለጀመሩትና የአህጉሩን ልማት ለሚያራምደው ጥረታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረጉ አመልክተዋል።

በፌዴራዊት የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ተመልካች ክፍል ተጠሪ ወይዘሮ ኡሺ አይትም የአፍሪቃውያኑ የራስ ጥረት ሊደአፍ እንደሚገባ በማስታወቅ፡ እኛ እናውቅልህአለን የሚሰኘው አዘውትሮ የሚሰማው የምዕራባውያኑ አባባል ወደ ጎን እንዲጣል አስገንዝበዋል። በአፍሪቃና በምዕራባዊው ዓለም መካከል ለተነቃቃው ትብብር መልካም ውጤት ያስገኛል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትንና በአሕፅሮት ኔፓድ የሚባለውን ለአፍሪቃ ልማት አዲሱ የአጋርነት ጉድኝትን አይት እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። ኔፓድ በርካታ አፍሪቃውያን መንግሥታት እአአ በ 2001 ዓም ያቋቋሙት ጉድኝት ነው። ኔፓድ በአህጉሩ የሚነሡ ውዝግቦችን አፍሪቃ በራስዋ አቅም መቆጣጠር፡ ማብቃት ወይም ከተቻለ ገና ሳይነሱ በፊት ማስወገድ የምትችልበትን ዘዴ ያዘጋጃል፤ በአፍሪቃውያቱ ሀገሮችም ውስጥ ዴሞክራሲያዊው መዋቅር የሚተከልበትንና ብዑላንን ወደ አህጉሩ መሳብ የሚቻልበትን ሁኔታ ያመቻቻል። ይሁንና፡ እአአ በ 1986 ዓም የሥነ ፅሑፍ የኖቤል ተሸላሚ የሆኑት የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ናይጀሪያዊው ዎሌ ሾይንካ ኔፓድን ዓይነቱ ትልቅ ጉድኝት ለአህጉሩ የሚበጅ ውጤት አያስገኝም በሚል የአይትን አባባል በተዘዋዋሪ መንገድ ተፃረዋል። ሾይንካ እያንዳንዱ አፍሪቃዊ መንግሥት ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ ልማት እንደሚያስፈልገው ቢያረጋግጡም፡ ይህን ገሀድ ለማድረግ፡ አህጉሩን እበለጠው የዕዳ ማጥና ችግር ውስጥ የሚያስገባው ግዙፍና የባዶ ዝና ፕሮዤ ሳይሆን የሚያስፈልገው ብዙ ትናንሽ ተቋማት መሆኑን ነው ያስረዱት። ወይዘሮ ኡሺ አይት ኔፓድን በተመለከተ ሾይንካ ያሳዩትን ጥርጣሬ ቢረዱትም፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ትልቅ የትብብር ጥምረት እንዲፈጠር የማድረጉ ጥረት ከግብ እስከደረሰ ድረስ ኔፓድ እንደሚሳካ አመልክተዋል።

በዓላማው ከአውሮጳ ኅብረት ጋር ተመሳሳይ የሆነው የአፍሪቃ ኅብረት በዚሁ ጥረቱ ላይ ከጀርመን መንግሥት ብዙ ድጋፍ እንደሚያገኝ ተስፋ ማድረጉን አይት አስረድተዋል። በአህጉሩ የሚነሡ ውዝግቦችን አፍሪቃ በራስዋ አቅም መቆጣጠር፡ ማብቃት ወይም ከተቻለ ገና ሳይነሱ በፊት ማስወገድ፡ የራስዋ ሰላም አስከባሪ ጓድ ማቋቋምና ዴሞክራሲያዊው መዋቅር መትከል ትችል ዘንድ ከአውሮጳ አሁን ከሚያገኘው የበለጠ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልገው የጀርመን ሥነ ጥበብና ፖለቲካ ተቋም ተጠሪ ሽቴፈን ማየር አስገንዝበዋል።