1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃውያን ስደተኞችና የእሥራኤል ውሳኔ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2004

እሥራኤል በሀገሯ የሚገኙ ወደ ስድሳ ሺህ የሚጠጉ አፍሪቃውያን ስደተኞችን ወደሀገራቸው ለመመለስ ውሳኔ አሳልፈች። በሕገ ወጥ መንገድ ወደ እሥራኤል የገቡት አፍሪቃውያን ስደተኞች ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ፈጥረውብናል በሚል

https://p.dw.com/p/15Crk
epa03124964 African refugees wait for a job offer near the central bus station in southern Tel Aviv, Israel, 27 February 2012. Some 50,000 Africans have entered Israel in recent years, fleeing conflict and poverty in search of safety and opportunity in the relatively prosperous Jewish state. A growing number of African migrants say they were captured, held hostage and tortured by Egyptian smugglers hired to sneak them into Israel. EPA/ABIR SULTAN
ምስል picture-alliance/dpa

ከእሥራኤል ሕዝብ እና ካንዳንድ የገዢው ፓርቲ አባላት ብርቱ ተቃውሞ ከተነሳ በኋላ ነበር ግፊት የጠነከረበት ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሚመሩት መንግሥት ከትናንት ወዲያ ይህን ውሳኔ የወሰደው። የሀይፋው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ እንደገለጸልን፡ በውሳኔው መሠረት፡ የመመለሱ ሂደት በሁለት ዙሮች የሚከናውን ሲሆን፡ በመጀመሪያው ዙር ወደ ሀገራቸው የሚመለሱት ስደተኞች ቁጥር ሀያ አምስት ሺህ ነው።


ግርማው አሻግሬ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ