1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃ ረሃቡና የጀርመን ዕርዳታ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 9 2003

የጀርመን መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ ላይ ለደረሰዉ ከባድ የረሃብ አደጋ የሚሰጠውን አስቸኳይ ዕርዳታ በእጥፍ ጨመረ።

https://p.dw.com/p/RaG5
ኬንያምስል Picture-Alliance/dpa

በአፍሪቃ ቀንድ በ 60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ የረሃብ አደጋ 10 ሚሊዮን ህዝብ መጋለጡን ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች ማስታወቃቸዉ አይዘነጋም። የጀርመን መንግስት ለዚህ ረሃብ አደጋ የሚሰጥዉን መጠን በአምስት ሚሊዮን ይሮ ከፍ ያደረገ ሲሆን፣ የእርዳታ ገንዘቡ በጀርመን እና በአለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች እንዲሁም በተ.መ.ድ የምግብ ፕሮግራም በኩል እንደሚሰራጭ የጀርመን የእርዳታ ድርጅት እና የዉጭ ጉዳይ መስራ ቤት አስታዉቀዋአል። የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለና የልማት ሚኒስትሩ ዲርክ ኒብል እንዳስረዱት ገንዘቡ በተግባር የሚውለው በተለይም ችግሩ ይበልጥ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚገኙ ስደተኞችን፣ ሴቶችንና ሕጻናትን ለመንከባከብ ነው። ነጻ ዴሞክራቱ ሚኒስትሮች ከዚሁ በማያያዝ የጀርመን ሕዝብም ረሃብተኛውን በግል መዋጮ እንዲደግፍ ጥሪ አድርገዋል። የአገሪቱ ቻንስለር ወሮ/ አንጌላ ሜርክል በበኩላቸው ባለፈው ማክሰኞ ኬንያን በጎበኙበት ወቅት ለስደተኛ መጠለያዎች አንድ ሚሊዮን ኤውሮ ዕርዳታ ለመስጠት ቃል መግባታቸው አይዘነጋም። የአፍሪቃን ቀንድ አካባቢ የመታው ድርቅ በሶማሊያ፣ በኢትዮጵ፣ በኬንያ፣ በጂቡቲና በኡጋንዳ የሰብል እጥረትንና የምግብ ዋጋ ንረትን ሲያስከትል 12 ሚሊዮን ገደማ የሚጠጋ ሕዝብን ለከፋ የረሃብ አደጋ ማጋለጡ የሚታወቅ ነው።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን