1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል የጦር ልምምድ ጀመረ

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ጥቅምት 8 2008

«ASF» በመባል የሚታወቀዉ የአፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል ዛሬ ልምምዱን ጀመረ። የአፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል ደቡብ አፍሪቃ ላይ የጀመረዉ ይኸው ልምምድ ለ20 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጦር ኃይሉ የፊታችን ታህሳስ 2015 ዓ,ም ሙሉ ሥራዉን እንደሚጀምርም ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/1Gqca
Eastern Africa Standby Force
ምስል DW/L. Ndinda

[No title]

የአፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል በምህጽረ ቃሉ «ASF» ወደ 25,000 ጦር ሰራዊት የያዘ ሲሆን በዛሬ ቀን የመጀመርያዉን የጦር ልምምድ በደቡብ አፍሪቃ ጀምሮአል። በጎርጎርሳዊዉ አቆጣጠር ከ2003 ዓ,ም ጀምሮ ለአፍሪቃ ችግር መፍቴሄ ይሆናል ተብሎ የተቋቋመዉ ይህ ኃይል በአፍሪቃ የጦርነት ቀዉሶችና፤ ሰላምን የሚያደፈርሱ ችግሮች ሲከሰቱ በአፋጣኝ ጣልቃ ለመግባትና ለማረጋጋት ሲባል መቋቋሙ ይታወሳል። ይህ የጦር ኃይል በአፍሪቃ ሕብረት ስር የአፍሪቃ ሰላምና ፀጥታ ንድፍ የጀርባ አጥንት መሆኑ ሲታወቅ፣ ልምምዱን ከአምስት ዓመት በፊት ለመጀመር ብያቅድም በብዙ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱ ይታወቃል። ለ20 ቀን የምቆየዉ ይህ ልምምድ እንደተጠናቀቀ በታህሳስ 2015 ሙሉ ስራዉን እንደምጀምር ነዉ የተገለፀዉ።


የአፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል «ASF» አምስት ብርጌድ ያቀፈ ስሆን፤ እነሱም የአፍሪቃ ዋና ክልላዊ ቡድኖች፣ ማለትም፣ የምዕራብ አፍሪቃ አገሮች፤ የኢኮኖሚ ማኃበረሰብ ታዛቢ ቡድን፤ በደቡብ አፍሪቃ የልማት ማኃበረሰብ፤ የመዓከላዊ አፍሪቃ አገሮች የኦኮኖሚ ማኃበረሰብ፣ የምስራቅ አፍሪቃ ቋሚ ኃይልና የሴሜን አፍሪቃ ክልላዊ አቅም፤ በመባል መዋቀራቸዉ ይታወቃል።


በአዲስ አበባ የጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስኪያጅና የአፍሪቃ ደህነት ፖሊስ ባለሞያ አምባሳደር ተፈራ ሻዉል የዚህን ክልላዊ ኃይሎችን ዋና ተልኮ አሰመልክቶ ለዶቼ ቬሌ ማብራርያ ሰጥተዋል። «የዚህ ቡድኖች መሰረታዊ ተግባር በማንኛዉም ግዜ ለኣገልግሎት ጥሪ ለሚደረግላቸዉ ወታደሮች ስልጠና መስጠትና ማዘጋጃት ነዉ። የተባበሩት መንግስታት ወይም አፍርቃ ኅብረት ወታደራዊ ኃይልን ስፈልግ፣ ጥያቄያቻዉን ወደምመለከተዉ አገሮች ይልካል፣ ከዚያም በመቀጠል አገሮች ከዚህ ከሰለጠኑትና ዝግጁ ከሆኑት ወታደሮች መርጦ ወደ ተልዕኮአቸዉ ቦታ ያሰማራቸዋል።»

Eastern Africa Standby Force
ምስል DW/L. Ndinda


የዓለም ዓቀፍ ፀጥታ ጥናት ተቋም ተንታኝ አቶ ሃሌሉያ ሉሌ እንደሚሉት፤ ይህ የጦር ኃይል መቋቋሙ ትልቅ ጠቀሜታ ያለዉ ነዉ ካሉ በዋላ፣ የፖለቲካና የባህል ዐዉድ ሃሳብ ዉስጥ በማስገባት ይህ ሃይል በራሳቸዉ ክልል ወይም በጎረበት አገሮች እንደሚሰማሩ አብራርቶዋል። የጀርመን ደንነት ባለሙያ የሆኑት ሰባስትያን ግሪፍ፣ ፕሮጀክቱ በገንዘብና በቁሳቁሶች እየረዱ ያሉት ጀርመንና ኣዉሮጳ ሕብረት መሆኑን ከስታወቁ በዋላ፣ እስካሁን ድረስ 27 ሚልዮን ዩሮ ከጀርመን 1.1 ሚልዮን ዩሮ ደግሞ ከኣዉሮጳ ሕብረት ማገኘታቸዉን ተናግረዋል። በተጨማሪም 750 ሚልዮን ዩሮ የአፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል «ASF» ኢንደምፈልግም አስረድተዋል።


እሄን ጉዳይ አስመልክቶ አቶ ሃሌሉያ ስያብራሩት፣ «ከኣዉሮጳ ኅብረትና ከአባል አገራት የምመጣዉ ገንዘብ ላይ ትልቅ ጥገኝነት አለ። ለአፍሪቃ ኅብረት ብቻ ሰይሆን ለስቪል ማህበረሰብ፣ ለሚዲያና ለዜጎችም ይህ ጉዳይ የምያሳስብ በመሆኑ የአፍርቃ ኅብረት የራሱን የገብ ምንጭ ኢንደምፈልግ ማድረጉ አስፈላጊ ነዉ።»


ይህ ጦር አፍሪቃ ዉስጥ ለሚከሰቱት ችግሮች መፍቴ ለማምጣትና የዉጭ ጣልቃ ገብነትን ይገታል፤ ተብሎ ቢታሰብም ገንዘብና ቁሳቁሶችን ከዉጭ መምጣቱ ጣልቃ ገብነቱን እንደማያስጥል ይገመታል።


መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ