1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃ ፣ አይሲሲ እና የአፍሪቃ ህብረት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 17 2009

ዙማ ሦስት የአፍሪቃ ሀገራት ከዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በምህጻሩ አይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ስለመወሰናቸው በሰጡት አስተያየት የድርጅቱ አባል መሆንም ሆነ ከአባልነት መውጣት የየሀገራቱ ሉዓላዊ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል ።

https://p.dw.com/p/2Rnmh
Pressekonferenz von Dlamani Zuma
ምስል DW/G. Tedla

Beri Pretoria(AU chairperson comment on Africans to leave ICC) - MP3-Stereo

የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ድላማኒ ዙማ አባል ሀገራት የፍትህ ስርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠየቁ ። ዙማ ሦስት የአፍሪቃ ሀገራት ከዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በምህጻሩ አይ..ሲ ለመውጣት ስለመወሰናቸው በሰጡት አስተያየት የድርጅቱ አባል መሆንም ሆነ ከአባልነት መውጣት የየሀገራቱ ሉዓላዊ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል ። አፍሪቃውያን በራሳቸው ፍርድ ቤት የሚዳኙበትን ስርዓት መጠናከእንደሚገባቸውም አሳስበዋል ። ደቡብ አፍሪቃ እና ብሩንዲ ባለፈው ሳምንት እንዲሁም ጋምብያ ደግሞ ከትናንት በስተያ ከአይሲሲ ለመውጣት መወሰናቸውን አስታውቀዋል ። የደቡብ አፍሪቃው ወኪላችን ዘገባ አለው ።

መላኩ አየለ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ