1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ የካቲት 29 2009

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀን ያደረገዉን መደበኛ ስብሰባ ትላንት ማጠናቀቁ ተዘገበ።

https://p.dw.com/p/2YqVb
Karte Äthiopien englisch

EPRDF vs. Opp. Pol. Party Negotiation - MP3-Stereo

በዘገባዉ መሠረት ከዋና የመወያያ ርዕሶች  አንዱ ኢህአዴግ በቅርቡ ከታቃዋሚ የፖለትካ ፓርትዎች ጋር የጀመረዉን ድርድር «በመገምገም በቀጣይ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ኮሚቴው አቅጣጫ» ያስቀምጣል የሚለዉ አንዱ ነበር። ዉይይቱን  በተመለከተ ከኢሕአዲግ ባለሥልጣናት  መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረታ ባይሳካም የተቃዋሚ ፖለትከኞችንና የተለያዩ ወገኖችን አስተያየቶች መርጋ ዮናስ አሰባስቧል።

ከታቃዋሞ ጎራ ያሉት ፖለትከኞች በአገርቱ ላለዉ የፖለትካ ቀዉስ «መፍቴዉ በኢህአዴግ እጅ ነዉ ይላሉ።በቅርቡ የተጀመረዉ ድርድር ለዉጤት እንዲበቃም ድርድሩን የ«እዉነት ማድረግ አለበት» ሲሉ አስተያየታቸዉን ይሰነዝራሉ።

የገዥዉ እና የተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች ተወካዮች  አራተኛዉ ዙሩን ድርድራቸዉን ባለፈዉ የካትት 24  እንዳጠናቀቁ ይታወሳል። ተቃዋሚዎችን ወክለዉ በስብሰባዉ ላይ የሚሳተፉት እስካሁን በስብስባዉ አለማዎች ላይ መስማማታቸዉንና ደስተኛ መሆናቸዉን ቢናገሩም ሌሎቹ ግን አሁንም ብዙ የሚያከራክሩ ነጥቦች እንዳሉ ገልፀዋል። 
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃም ኮምቴ ስብሰባ ሚስጥራዊ በመሆኑ መረጃ ለማግኘት እንደሚከብድ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልፀዉ። ፓርቲያቸዉ ከኢህአዴግ ስብሰባ የሚጠብቀዉን እንደሚከተለዉ ይገልፁታል።

የገዥዉን ፓርቲ ርምጃ እና አቋም እንዴት ትመለከቱታላችሁ ብለንም ከአድማጮቻችን አስታያየት ጠይቀን ነበር። ሳዉድ አራብያ እንደሚኖሩ የምናገሩት አቶ ታደሰ ሲሳይ «ድርድሩ የይስሙላ ነዉ» ይላሉ።

በዚሁ ርዕስ ላይ የዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ደረ ገፅ ተከታታዮችንም አወያይተን ነበር።  አቶ ቢንያም ጌታቸዉ በሚል የፌስቡክ ስም የያዙት ግለሰብ «አንድም የምርጫ ጣቢያ ላይ ያለሸነፉ ተቃዋሚዎች እንዴት ህዝብን ወክለው ይደራደራሉ? ሲሉ ጠይቀዋል። አቶ አለሙ የተባሉት ደግሞ «ተቃዋሚ ፓርቲዎች የእንደራደር ጥያቄውን መቀበላቸዉ ከምንም በላይ በሰላማዊ ትግል ማመናቸዉን ያሳያል፣ ስለዚህ ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች «ለመደራደሪያነት ያቀረቧቸውን ነጥቦች መርምሮ ለሃገር ጉዳት ከሌላቸው ተቀብሎ መስማማት ይኖርበታል» ይላሉ። አቶ ጅሩ አዱኛ የተባሉት ደግሞ «የገዥው ፓርቲ አቋም እድሜውን ለመረዘም የምደረግ ጥረት ነው፡፡ መንግሥት የህዝቡን ጥያቄ አንድም አልመለሰም፣ ጠንካራ የሚበሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እያሰረ፣ እራሱ ዳኛ፣ እረሱ አራጋቢ፤ እራሱ ተጫዋች»  ነዉ  ሲሉ ትችታቸዉን ሰንዝረዋል።

ስለስብሰባው ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ