1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራንና የእስራኤል ስጋት

ሐሙስ፣ ጥር 12 2008

ኢራን አዘናግታ በ 10 ና 15 ዓመታት ጊዜ ዉስጥ በጦር ኃይል ተደራጅታ የኒኩልየር ቦንብ ሰርታ ብቅ ማለትዋ አይቀሬ ነዉ ብለዉ ወታደራዊ መኮንኖቹ መላምታዊ ስጋታቸዉን እያሰሙ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1HhrH
ምስል GIL COHEN MAGEN/AFP/Getty Images

[No title]

የኢራንና የምዕራብ መንግስታት መቀራረብ እስራኤልን ኃሳብ ላይ ጥሎአታል። የእስራኤል የወታደራዊ ጠበብትና የአገሪቱ የጦር ጀነራሎች ቋሚና ዘላቂ ስትራቴጂ ይነደፍ ብለዉ የአገሪቱን ፖለቲከኞች አጥብቀዉ እየወተወቱ ነዉ። ኢራን አዘናግታ በ 10 15 ዓመታት ጊዜ ዉስጥ በጦር ኃይል ተደራጅታ የኒኩልየር ቦንብ ሰርታ ብቅ ማለትዋ አይቀሬ ነዉ ብለዉ ወታደራዊ መኮንኖቹ መላምታዊ ስጋታቸዉን እያሰሙ ነዉ። ይህን የእስራኤልን ስጋት በተመለከተ የዶቼ ቬለዉ ክርስትያን ቫግነር ከቴላቪቭ የዘገበዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል እንዲህ ያቀርበዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሠ