1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና የዓለም ንግድ ድርጅት ዓባልነት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 22 2001

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ዓባል ለመሆን ካመለከተች ወዲህ አምሥት ዓመታት አለፉ። ድርድሩ ውስብስብና ጊዜ የሚፈጅ እንደሚሆን ነው የሚታመነው።

https://p.dw.com/p/HgXE
ምስል AP GraphicsBank/DW

የዛሬው እንግዳችን አቶ መላኩ ገበይ ደስታ በመምሕርነት ሥራቸውም ሆነ በሚያካሂዷቸው ጥናቶች በተለይ በዓለም ንግድ ሕግ ላይ ነው የሚያተኩሩት። ከድርጅቱም ጋር ብዙ አብረው ይሰራሉ። በስኮትላንድ ዳንዲይ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምሕር ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የድርጅቱ ሕግ በንግድና በዕድገት ረገድ ምን ሚና እንዳላቸው በማጥናት፤ በመመርመር ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ዓባል ለመሆን ባላት ፍላጎት፣ በድርድሩ ሂደት፣ ዓባልነቱ ሊያስከትል በሚችለው ጥቅም ወይም ጉዳት፤ በአጠቃላይ በድርጅቱ ባሕርይ ላይ አነጋግረናቸዋል።

መሥፍን መኮንን፣

ተክሌ የኋላ፣