1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና የ 2007 ምኞትና ተስፋ

እሑድ፣ መስከረም 4 2007

ጊዜ ይከንፋል ፣ ትውልድ ያልፋል ፣ ትውልድ ይተካል። ሁሉም ሰው በዝች ዓለም በጤና፣ በሰላም፣ በተድላና ፍስሐ መኖር ይፈልጋል። ለራሱና ለሀገሩ ለሚገኝበት ማሕበረሰብ ፣ በጎ ነገር ፣ ሰላምና ብልጽግና ይመኛል። ምኞት አይከለከልምና ሰው ብዙ ሊመኝ ይችላል። እርግጥ የሚሣካና የማይሣካ የምኞት ዓይነት ይኖራል።

https://p.dw.com/p/1DBu0
ምስል AP

በማሕበራዊ ኑሮ፣ የትናንቱ ተግባር ለዛሬውና ለነገው መሠረት ነው። ዛሬ ይበልጥ አዎንታዊ የሆኑ ድርጊቶችንና ሁኔታዎችን ለማየትና ወደፊት እየተጓዝን ያለንበት ፍኖት ምን ያህል ብሩሕ ነው? ብሎ ማሰላሰልም ፤ መጠየቅም አይቀርም። ያም ሆኖ «ቸር ተመኝ፣ ቸር ታገኝ» ነውና ምሳሌው፣ በጎ ነገር ያጋጥማል ብሎ መመኘት በጎ ነው።

ኢትዮጵያውያን ምን ቢደረግ፣ በጎ ምኞታቸው የመሣካት ዕድል ይገጥመዋል?የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሂደት በተለያዬ መልኩ በመዳሰስ፤ ፤ ተጨባጭ ሁኔታ ፣ ምኞትና ተስፋ እንዴት ሊጣጣሙ እንደሚችሉ ሐሳባቸውን ያካፍሉን ዘንድ ለዛሬው ውይይታችን 3 እንግዶች ጋብዘናል።

ተክሌ የኋላ

ልደት አበበ