1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉን ሥደተኞች ሞትና ስቃይ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 26 2002

እስካሁን አስራ-አንዱ ለሞት፥ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ሌሎችን ለበሽታ እና የተቀሩትን በሙሉ ለስቃይ የዳረገዉ ችግር የሚወገድበት ብልሐት አሁንም ግልፅ አይደለም

https://p.dw.com/p/P1uR
ጀልባዋ-ሠላም ትገባ ይሆናል ግን እስር ቤትም ሞት አለምስል AP

የስዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎች ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ካሰሯቸዉ ኢትዮጵያዉያን መካካል ጂዘን ዉስጥ አምስቱ ከነሱ በፊት ጂዳ ዉስጥ ደግሞ ሌሎች ስድስት መሞታቸዉ በትናንቱ ዜናችንና ከዚያም በፊት ተዘግቧል።ምክንያቱ የእስር ቤቱ ሙቀትና መጨናነቅ ነዉ።የሰዎቹ መሞት ከመሰማቱ በፊት ስደተኞቹ የታሠሩበት ቦታ ለሕይወታቸዉ አደገኛ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ዘግበንም ነበር።ይሁንና እስካሁን አስራ-አንዱ ለሞት፥ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ሌሎችን ለበሽታ እና የተቀሩትን በሙሉ ለስቃይ የዳረገዉ ችግር የሚወገድበት ብልሐት አሁንም ግልፅ አይደለም።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ያነጋገራቸዉ በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስልና የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ተጠሪዎች ግን ጉዳዩን እየተከታተልን ነዉ ይላሉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ