1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን

ማክሰኞ፣ መስከረም 17 2009

ኢትዮጵያዉያን ጨምሮ 220 አፍሪቃዉያን ስደተኞችን ትናንት ወደ የሃገራቸዉ መመለስዋን የየመን ባለስልጣናት ገለፁ። የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ ባወጣዉ ዘገባ መሰረት የመን ወደየሃገራቸዉ ከመለሰቻቸዉ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ በደቡባዊ የኤደን ወደብ ከተማ የነበሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ናቸዉ።  

https://p.dw.com/p/2QdpG
Flüchtlinge Boot Symbolbild Jemen Äthiopien
ምስል picture-alliance/dpa/Xinhua /Landov

Jemen_abschiebung afrikanische immigrants_Äthiopiens/mmt - MP3-Stereo

 

 

የየመን ባለስልጣናት በገለፁት መሰረት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 220 ስደተኞች ከመጡበት ከሶማልያ በኩል የተመለሱት በኤደን ባህር በኩል በመርከብ ተጭነዉ ነዉ። በየመን ሰንዓ የሚገኘዉ ተባባሪ ወኪላችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት ስደተኞቹ የተመለሱት ባለፈዉ ረቡዕና ቅዳሜ እለት ነዉ፤ የሚመለሱትም በዉዴታ ነዉ ሲል ገልጾአል።  በየመን

Jemen Flüchtlinge Gewalt 08.07.2014
ምስል picture-alliance/dpa

የሚታየዉ ረሃብና ጦርነት ካለዉ ሁኔታ ጋር ተዳምሮም ሁኔታዉ አሳሳቢ መሆኑን ነዉ ግሩም ተናግሮአል። በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት «IOM» የኮሙኒኬሽንስ ጉዳይ ባለሞያ አቶ አለማየሁ ሠይፈስላሴ ሰሞኑን ከየመን የተመለሰ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ አለመኖሩን ነገር ግን፤ ከጅቡቲ ወደ ሰባ ኢትዮጵያዉያን መመለሳቸዉን ተናግረዋል።  

ወደ ሀገራቸዉ ለመመለስ የሚፈልጉ ከ 2000 በላይ ኢትዮጵያዊያን የመንዉስጥ እንዳሉ የተናገሩት አቶ አለማየሁ ሠይፈ ስላሴ መሥርያ ቤታቸዉ በቀጣይ እነዚህን ዜጎች ለመመለስ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።    

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ