1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉያን በሳዉዲ

ዓርብ፣ ጥቅምት 6 2002

ሰራተኞች በህጋዊ መንገድ ወደሳዉዲ አረቢያ የሚሄዱበት ዉል መፈረሙ በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ከተነገረ አንስቶ በርካታ ኢትዮጵያዉን ህጋዊ የስራ ዉል በመፈራረም መሄድ ከጀመሩ አንድ ዓመት እየተገባደደ ነዉ።

https://p.dw.com/p/K8Sq
ምስል AP

የሳዉዲ ከፍተኛ የህግ አርቃቂና አስፈፃሚ አካል የአሹራ ምክር ቤት የቤት ሰራተኞችን መብት የሚከላከዉን ህግ መደንገጉ በኗሪዉ ዘንድ ደስታ መፍጠሩንም በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል። ህጉ ለሰራተኞች ሊከበሩ የሚገቡ መብቶችን ዘርዝሮ የደነገገ ቢሆንም ዛሬም በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ኢትዮጵያዉያን በደል እየደረሰባቸዉ ለመብታቸዉ የሚከራከር እንዳጡ ይናገራሉ። በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ የበኩሉን እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ነብዩ ሲራክ /ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ