1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያንን ከየመን የማውጣቱ ጥረትና አይ ኦ ኤም

ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2007

IOM ፣ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ዜጎችን ከየመን በአውሮፕላን የማውጣቱን ሥራ ለጊዜው መቋረጡን አስታወቀ ። የIOM የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዓለማየሁ ሰይፈ ሥላሴ የሰንዓው አውሮፕላን ማረፊያ ባለፈው ማክሰኞ ከተደበደበ በኋላ IOM ያቀዳቸው መሰል በረራዎች ለጊዜው እንዲቆሙ መደረጉን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1FMw4
Jemen Luftangriff auf Sanaa
ምስል Reuters/K. Abdullah

ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM ኢትዮጵያውያንን ጦርነት ከሚካሄድባት ከየመን ለማስወጣት የሚያደርገውን ጥረት መቀጠሉን አስታውቋል ። የIOM የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዓለማየሁ ሰይፈ ሥላሴ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ከሚያዚያ አንስቶ ኢትዮጵያውያንን ከየመን ወደ ሃገራቸው መመለስ ጀምሯል ። ድርጅቱ ከየመን ከመለሳቸው ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ ወደ ሃገራቸው በአውሮፕላን የተወሰዱት 77 ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ። ከማክሰኞ በኋላም IOM ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የውጭ ዜጎችን በአውሮፕላን ከየመን ለማስወጣት ቢያቅድም አቶ አለማየሁ እንደተናገሩት ሥራውን መቀጠል አልቻለም ።

አቶ ዓለማየሁ እንደሚሉት IOM እስካሁን ከሰንአ የመን፣የተወሰኑ ኢትዮጵያውያንን በካርቱም ሱዳን በኩል ወይም በቀጥታ በአውሮፕላን ወደ ሃገራቸው ሲመልስ ቆይቷል ።ኢትዮጵያኑ በሌላ ሃገር በኩል ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ሲደረግ ደግሞ ችግሮች ማጋጠማቸው አልቀረም ይላሉ አቶ ዓለማየሁ ።
IOM 2
የውጭ ዜጎች ከየመን በመውጣት ላይ ያሉት በጀልባዎችም ጭምር ነው ።በጀልባ የሚነሱት መድረሻ ደግሞ ጅቡቲ ናት ።
ድምፅ IOM 4
IOM ከየመን ጅቡቲ የገቡትንና ከጅቡቲም ወደ የመን ለመሄድ አስበው መውጫ አጥተው እዚያ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያውያንም እየመለሰ መሆኑን አቶ ዓለማየሁ ተናግረዋል ። አቶ ዓለማየሁ እንዳሉት በሚያዚያ ወር ብቻ ድርጅቱ ከየመንና ከጅቡቲ የመለሳቸው ኢትዮጵያውያን 494 ናቸው ።ከጅቡቲ ከተመለሱት 99 ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ 25 ታዳጊ ወጣቶች ይገኙበታል ።አቶ ዓለማየሁ ከአንድ ሳምንት በፊት የተቋረጠው ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የውጭ ዜጎችን ከየመን የማስወጣቱ ጥረት የሃገሪቱ ፀጥታ አስተማማኝ እንደሆነ በቅርቡ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል ።

Jemen Luftangriff auf dem Flughafen in Sanaa
ምስል AFP/Getty Images/M. Huwais
Jemen Luftangriff auf dem Flughafen in Sanaa
ምስል AFP/Getty Images/M. Huwais

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ