1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን በሊቢያ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2003

በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው 20 የሚጠጋ አገር መልቀቅ ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን ትሪፖሊ ይገኛሉ።ያሉበት ሁኔታአስከፊ እንደሆነ ገልፀውልናል።

https://p.dw.com/p/Ri5F
የሊቢያ ጦርነትምስል dapd

የአለም አቀፉ የፍልሰት ጉዳይ ተመልካች ድርጅት መምህፃሩ IOM የተኮናተረው አንድ የስደተኞች መርከብ ትሪፖሊ መድረሱን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዣን ፊሊፕ ቻውንዚ ዛሬ ለጀርመን የመገናኛ ብዙኻን DPA አስታወቁ። መርከቡ ቀደም ብሎ ይደርሳል ተብሎ ቢጠበቅም በአንዳንድ ከተሞች በነበረው ከፍተኛ ጦርነት ትሪፖሊ ባህር ጠረፍ ለመድረስ ብዙ ጊዜ ወስዶበታል። በትሪፖሊ በርካታ ግብፃዊያን ሊቢያን ለቀው ለመውጣት እየተጠባበቁ ነው። IOM ከጀርመን በተኮናተራቸው በርካታ መርከቦች አማካኝነት 8300 ስደተኞችንና የቆሰሉ ሰዎችን ሊያስወጣ ችሏል። በአሁኑ ሰዓት አገር መልቀቅ ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን ትሪፖሊ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ሁለቱን ልደት አበበ ለማነጋገር ችላለች።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ