1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን በካን የፊልም ፌስቲቫል

ዓርብ፣ ግንቦት 22 2006

በፈረንሣይዋ ጥንታዊት ከተማ ካን ውስጥ ዘንድሮ በተከናወነው ዓመታዊ የካን ፊልም ፌስቲቫል ለመታደም በፊልም ሙያ የተሰማሩ አምስት ኢትዮጵያውያን ወደ ስፍራው አቅንተው ነበር፤ አራት ሴቶች እና አንድ ወንድ።

https://p.dw.com/p/1C8an
ምስል Reuters

ያምሮት ንጉሤ፣ ሔርሞን ኃይላይ፣ ሕይወት አድማሱ፣ አዳነች አድማሱ እና ዳንኤል ደበበ ናቸው ታዳሚያኑ። የካን የፊልም ፌስቲቫል፤ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በፊት ሲቋቋም፣ ለሲኒማ ጥበብ እድገት አስተዋፅዖ ያደረጉ ባለሙያዎችን እና ሥራዎቻቸውን በማስተዋወቅ ሲኒማን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማክበር በሚል መርኅ ነው። እጎአ በ1946 ዓም የተቋቋመው ይኽ የካን የፊልም ፌስቲቫል በየዓመቱ ሲከበር ዘንድሮ 67ኛ ዙር ላይ ደርሷል። በእዚህ የፊልም ፌስቲቫል የተሳተፉት አምስቱም ኢትዮጵያውያን ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ነው።

የካን የፊልም ፌስቲቫል ቀዩ ምንጣፍ
የካን የፊልም ፌስቲቫል ቀዩ ምንጣፍምስል Reuters

ከግንቦት 6 ቀን፣ 2006 ዓም ለ12 ተከታታይ ቀናት በተከናወነው የፊልም ፌስቲቫል ኢትዮጵያውያኑ ለአንድ ሣምንት ያህል በመታደም የተለያዩ ሥልጠናዎችን አግኝተዋል። በፌስቲቫሉ ለመሳተፍ ከ40 በላይ ኢትዮጵያውያን አመልክተው እንደነበር የውድድሩ አዘጋጆች እንደገለፁላቸው ኢትዮጵያውያኑ ታዳሚያን አጫውተውናል።

ወደፊት ሌሎች ኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎች እና ሠራተኞችም በእንደዚህ አይነት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ለመሳተፍ ጥረት እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማጫወቻ ይጫኑ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ