1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  ኢትዮጵያ ባስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 8 2009

ሕዝቡም አዋጁ ሥላስፈራዉ እርስበርሱ የሚያደርገዉን ግንኙነት፤ ዉይይትና እንቅስቃሴዉን በጅጉ ቀንሷል። የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡም በተለይ ወጣቱ መረጃ የሚለዋወጥበትና አዳዲስ መረጃዎች የሚያገኝበት መንገድ ተዘግቷል

https://p.dw.com/p/2RO5L
Äthiopien Trauer für gestorbenen Demonstranten
ምስል picture-alliance/AP Photo/K. Prinsloo

(Q&A) Addis after the Emergency Law - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግስት ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በተለይ ደግሞ የአዋጁ  የአመፈፃጸም መመሪያ ያለዉን ደንብ ካስታወቀ ወዲሕ የሀገሪቱ ጦር ኃይልና ፖሊስ በሕዝቡ ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር፤ ፍተሻ እና ገደብ በጅጉ ተጠናክሯል። ፀጥታ አስከባሪዎች የሚጠረጥሯቸዉን ሰዎች ያስራሉ፤ እንቅስቃሴዎቻቸዉን ያዉካሉም። ሕዝቡም አዋጁ ሥላስፈራዉ እርስበርሱ የሚያደርገዉን ግንኙነት፤ ዉይይትና እንቅስቃሴዉን በጅጉ ቀንሷል።የኢትተርኔት አገልግሎት በመቋረጡም በተለይ ወጣቱ መረጃ የሚለዋወጥበትና አዳዲስ መረጃዎች የሚያገኝበት መንገድ ተዘግቷል። አዲስ አበባ ሕዝብን እንቅስቃሴ በተመለከተ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ