1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፣ ተቃውሞ እና ኢንቬስትመንት

እሑድ፣ መስከረም 8 2009

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ተቃውሞ እና ግጭት በርካታ ሰዎች በጸጥታ ኃይላት ተገድለዋል፤ የውጭ ሃገራት ንብረቶች ላይም ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1K3pp
Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል Solomon Mengist

ኢትዮጵያ፣ ተቃውሞ እና ኢንቬስትመንት

ኢትዮጵያ ካለፉት ዓመታት ወዲህ ጠንካራ የኤኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች መሆኗን መንግሥት እየገለጸ ነው። ለዚሁ እድገትም የአገር ውስጥና የውጭ ባለወረቶች መሰማራት ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከተ ይገልጣል። ይሁንና፣ ካለፉት በርካታ ሳምንታት ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የታየው ተቃውሞ እና ግጭት ከተለያዩ ዘርፎች ጎን፣ በኤኮኖሚው እንቅስቃሴም ላይ ተፅዕኖ ማስከተሉን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ተቃውሞ እና ግጭቱ በወረት ፍሰት እንቅስቃሴ፣ በተለይም፣ በውጭው ኢንቬስትመንት ላይ ሊያሳርፈው የሚችለው ወይም ያሳረፈው ተፅዕኖ ሰሞኑን እያነጋገረ ነው።

ሙሉውን ውይይት ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማጫወቻ ይጫኑ።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ