1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ እና የአውሮጳ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሚና

ረቡዕ፣ ግንቦት 11 2002

ከአራት ቀን በኋላ፡ ግንቦት አስራ አምስት፡ 2002 ዓም የሚካሄደውን አራተኛው አጠቃላይ ምርጫ በታዛቢነት ከሚከታተሉት ቡድኖች መካከል አንዱ አንድ መቶ ሀምሳ አባላት ያሉት የአውሮጳ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ነው።

https://p.dw.com/p/NRue
ምስል DW

እንደሚታወሰው፡ ህብረቱ በ 1997 ዓም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ምርጫም እንዲታዘብ የላከው አንድ ሌላ ቡድን ያኔ ከምርጫው በኋላ ያወጣው ዘገባ የኢትዮጵያን መንግስት እና ህብረቱን ሲያወዛግብ ነበር። በዚህም የተነሳ የዘንድሮውን ምርጫ ለመታዘብ በሀገሪቱ የሚገኘው የህብረቱ ቡድንን ሚና በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ጥርጣሬ እንደነበረው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ሉድገር ሻዶምስኪ በአዲስ አበባ ያነጋገራቸው የአውሮጳ ህብረት ቡድን መሪ ሚስተር ቲስ ቤርማን ገልጸዋል።

አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ