1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ከተማ ቦታ አዋጅና ተቃዉሞዉ

ሐሙስ፣ ጥር 17 2004

የኢሕአዲግ መንግሥት ያወጣዉ አዋጅ መንግሥትን ባለርስት የኢትዮጵያ ሕዝብን ደግሞ ገባር ወይም ጪሰኛ የሚያደርግ ነዉ

https://p.dw.com/p/13qg7
ምስል picture alliance/dpa



የኢትዮጵያ መንግሥት የከተማ ቦታን በኮንትራት (በሊዝ) ለማከራየት ያወጣዉን አዋጅ የሐገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አጣጥለዉ ነቀፉት።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ የአንድነት መድረክ እንደ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫና ባለሥልጣናቱ በየፊናቸዉ በሰጡት አስተያየት እንዳስታወቁት የኢሕአዲግ መንግሥት ያወጣዉ አዋጅ መንግሥትን ባለርስት የኢትዮጵያ ሕዝብን ደግሞ ገባር ወይም ጪሰኛ የሚያደርግ ነዉ።አዲሱን ሕግ ከዚሕ በፊትም የተለያዩ ወገኖች አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል። መንግሥት ግን ሕጉ ለደሐዉ ጠቃሚ ነዉ ባይ ነዉ።

ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ