1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፡ ኬንያ እና አወዛጋቢው የግልገ ጊቤ ግድብ ስራ ምክክር

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2001

የኃይል እጥረት ኤኮኖሚዋን አብዝቶ የጎዳት ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችሉ ግድቦችን በመስራት ላይ ትገኛለች።

https://p.dw.com/p/I2rI
ምስል picture-alliance / dpa

በአስራ ሰባት ነጥብ ስድስት ቢልየን ዶላር በመገንባት ላይ ባለው አንድ ሲህ በባ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ በታሰበው የግልገል ጊቤ ግድብ ቁጥር ሶስት ከተለያየ አካባቢ የተለያየ ተቃውሞ እየቀረበ ነው። ግድቡ ያካባቢውን ስነ ምህዳር ያዛባል፡ በኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ታችኛው ክፍል የሚኖረውን አርብቶ አደርም ህይወትን አደጋ ላይ ይጥለዋል ከሚሉት መካከል አንድዋ ኬንያ ናት። በዚሁ የግድብ ጥናት ላይ የሁለቱ ሀገሮች ከፍተኛ አመራር አባላት ዛሬ በአዲስ አበባ ምክክር ጀምረዋል። ታደሰ እንግዳው