1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፤ የምርጫ ዝግጅትና ዉዝግብ

እሑድ፣ የካቲት 29 2007

ምርጫዉን በበላይነት የሚመራዉና የሚያስተባብረዉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ አላማ አስፈፃሚ ነዉ ከሚለዉ ጀምሮ፤ ቦርዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይከፋፍላል፤ ከተከፋፈሉ ፖለቲከኞች ላንዱ ሕጋዊ ዕውቅና እየሰጠ ሌላዉን ይነፍጋል፤ የምርጫ ሕግን በመፃረር ዕጩዎችን በዕጣ እለያለሁ በሚል የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች በዉድድሩ እንዳይቀርቡ አግዷል።

https://p.dw.com/p/1EmuM
ምስል DW

ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ግንቦት ለሚደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ ዝግጅቱ በየመስኩ መቀጠሉ ሲዘገብ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሥሞታ፤ቅሬታና ወቀሳ፤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መልስና ማስተባባያ ተደጋግሞ እየተሰማ ነዉ።በአብዛኞቹ አዳጊ ሐገራት ምርጫ በተቃረበና በተደረገ ቁጥር የገዢ ፓርቲዎችና የተቃዋሚዎችን፤የፖለቲካ ፓርቲዎችና የአስመራጭ ተቋማትን፤ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የመንግሥት ባለሥልጣናትን አልፎ ተርፎ የእጩ ተፎካካሪዎችና የታዛቢዎችን ዉዝግብ መስማት እንግዳ አይደለም።

ኢትዮጵያም እስካሁን አንዴም ከዉዝግብ፤ ወቀሳ፤ ክስና ትችት የፀዳ ምርጫ አስተናግዳ አታዉቅም።የዘንድሮዉም ዉዝግብና የዉዝግቡ ምክንያቶች፤ በተለይም የሕግ፤ የአስተዳደር፤ የገለልተኝነት ጥያቄዎች ጠንከር ያሉ ይመስላሉ።

ምርጫዉን በበላይነት የሚመራዉና የሚያስተባብረዉ ብሕራዊ ምርጫ ቦርድ የገዢዉ ፓርቲ የኢሐዴግ አላማ አስፈፃሚ ነዉ ከሚለዉ ጀምሮ፤ ቦርዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይከፋፍላል፤ ከተከፋፈሉ ፖለቲከኞች ላንዱ ሕጋዊ ዕውቅና እየሰጠ ሌላዉን ይነፍጋል፤የምርጫ ደንብና ሕግን በመፃረር ዕጩዎችን በዕጣ እለያለሁ በሚል የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች በዉድድሩ እንዳይቀርቡ አግዷል።ለምርጫ ቅስቀሳ በቂ የመገናኛ ዘዴዎች ጊዜ አልመደበም የሚሉ እና ብዙዎች ናቸዉ።ሁሉንም ማንሳት አንችልም።ይሁንና በዛሬዉ ዉይይታችን ዋና ዋናዎችን አንስተን ባጫጭሩ ለመቃኘት እንሞክራለን።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ