1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፦ የምርጫ ዝግጅት፦የፖለቲከኞች ግድያና ዉዝግብ

ሰኞ፣ ግንቦት 2 2002

የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ መልስ-መረር-ከረር ያለም ነዉ።በግድያ የሚታወቀዉ-ኢሐአዲግ እንጂ መድረክ አይደለም የሚል። የእስካሁኑ ዉዝግብ ወቀሳዉ ከግድያ ደርሷል።ግድያዉ በፋንታዉ ለፖለቲከኞች ሌላ መወዛገቢያ ለሕዝቡ ግን በርግጥ የሥጋት ምንጭ ሊሆን ይችላል።

https://p.dw.com/p/NKWs
ከፊል አዲስ አበባምስል Peter Zimmermann

10 05 10

ድምፅ

አቶ ሽመልስ ከማል-የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ።
ድምፅ

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተባባባሪ ሊቀመንበርና የመድረክ ከፍተኛ ባለሥልጣን።ክርክር ዉዝግብ፥ግድያ ወቀሳዉ እንደቀጠለ-የምራጨዉ ዕለትም ደረስኩ አለ።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የኢትዮጵያ ምርጫና እና የፖለቲከኞች ግድያ፥ ዉዝግብ የዛሬ ርዕሳችን ነዉ።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።

የካቲት ላይ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) አባልና ፓርቲዉን ወክለዉ በትግራይ ክልል ለምክር ቤት እንደራሴነት ይወዳደሩ የነበሩት የአቶ-አረጋዊ ገብረ ዩሐንስ-ግድያ አነጋግሮ ሳበቃ፥እዚያዉ ትግራይ ዉስጥ ኢትዮጵያን ከኤርትራ በምታዋስነዉ አነስተኛ ከተማ የደረሰ የቦምብ ፍንዳታ አምስት ሰዎችን ገድሎ ሌሎችን ማቁሰሉ ሥለ ግንቦቱን ምርጫ ሰላማዊ ሒደት በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ሌላ ጥያቄ-አክሎ መጋቢት ተጋመሠ።

Flagge Äthiopien
ምስል AP

የኢትዮጵያ መንግሥት በርግጥ የአቶ አረጋዊ ገዳዮች መያዛቸዉን፥ ለፍርድ መቅረባቸዉንም አስታዉቋል።በቦምብ ፍንዳታዉ የኤርትራ እጅ አለበት ብሎ መጠርጠሩንም መንግሥት ገልጧል።ግን ሥለ ምርጫዉ ሰላማዊ ሒደት የሚነሳዉን ጥያቄ ዳግም-የሚያስጠይቅ-ሁነት ተከሰተ።ምዕራብ ሸዋ ዉስጥ አንድ ወጣት ፖለቲከኛ ተገደሉ።
ገዳይ-የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በሽታ ነዉ።ሟቹም የገዢዉ ፓርቲ አባል ነበሩ።የዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የመድረክ ባለሥልጣናት ግን ያኔም-ያሉት፥ አሁንም የሚሉት ተቃራኒዉን ነዉ።አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬም ደገሙት።
ግድያዉ እንዳሟገተ ሚያዚያ ሊሰናበት ዕለታት ሲቀሩት የንግሥት መግለጫ ወጣ።ምዕራብ ሽዋ ኢሉ ገላን ወረዳ-ስምንት የመድረክ አባላት ወይም ደጋፊዎች አንድ የኢሕአዲግ አባልን ለመደብደብ ዘምተዉ ሰዉዬዉን ሲያጡ አባትና ወንድሙን ደበደቡ ይላል-መግለጫዉ። በማከታተል የመድረክ አባላት ወይም ደጋፊዎች እዚያዉ ምዕራብ ሸዋ ዉስጥ ዳኖ ወረዳ ኢታና ኢዶሳ የተባሉ የኢሕአዴግ እጩ ተወዳዳሪን ገደሉ በማለት መንግሥት ወቀሰ።

መንግሥት ተቃዋሚዎችን በነብሰ-ገዳይነት ሲወነጅል የኢታና ኢዶሳ ግድያ የመጀመሪያዉ ነበር።ወቀሳዉ ሲያወዛግብ-ባለፈዉ ሳምንት ባሌ ዉስጥ አዳባ ከተማ በተሰበሰቡ ሰዎች መሐል ቦምብ ፈንድቶ-ሁለት ሰዎች ሞቱ።አስራ-አራት ያሕል ቆሰሉ።

ቦምቡ የተጣለዉ የኢሕአዲግ አባል የሆነዉ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) የተመሠረተበትን ሃያኛ አመት በአል ለማክበር በተሰበሰሰበ ሕዝብ መሐል ነዉ።የመንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከመል እንዳሉት የቦምብ ጣዮቹ አላማ በበአሉ ላይ የተገኙትን የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዝዳት አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድን ለመግደል ነበር።ምክትል ፕሬዝዳንቱ የደረሰባቸዉ ጉዳት የለም፥ ሰወስት ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል።
በማግስቱ አርብ እዚያዉ ደቡብ ኦሮሚያ ዉስጥ ሐሰን ረጋሳ የተባሉ የፖሊስ ባልደረባ በጩቤ ተገደሉ።ቃል አቀባይ ሽመልስ ከማል ከአደባዉ የቦምብ ፍንዳታ በስተቀር ለሌሎቹ ግድያዎች ተጠያቂዎቹ የመድረክ አባላት ናቸዉ ባይ ናቸዉ።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ግን ወሬዉ ብዙ ነዉ-ይላሉ።በተጨባይ የሚያዉቁት ግን አንድ ነገር ነዉ።በፓርቲያቸዉ ላይ የሚሰነዘረዉን ወቀሳ ሐሰትነት።
መድረክም መንግሥትን ይወቅሳል።እንደገና ወደ ሚያዚያ፥ እንደገና ወደ ትግራይ-ዉቅሮ ማራይ በተባለዉ የምርጫ- ክልል መድረክን ወክለዉ በሚወዳደሩት በአቶ አያሌዉ በየነ ቤት ላይ ሁለት የእጅ ቦምቦች ተጥለዉ ነበር።ከሁለቱ አንዱ ቦምብ አልፈነዳም።የፈነዳዉም በሰዉ ሕይወት ላይ ያደረሰዉ ጉዳት የለም።ሰሐርቲ ሳመረ በተባለዉ ምርጫ ክልል መድረክን ወክለዉ የሚወዳደሩት አለቃ ትርፈ ሐዲሽ አንዲት የኢሕአዲግ ካድሬ ባስተባበሯቸዉ ልጆች መደብደባቸዉን መድረክ አስታዉቆ ነበር።

Karte von Äthiopien
ምስል AP GraphicsBank/DW

የአካባቢዉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወቀሳዉን አልተቀበሉትም።ቃል-አቀባይ ሽመልስ ከማል ወቀሳዉ መኖሩን አልካዱም።ግን መሠረተ ቢስ-ነዉ-ይሉታል።እንዲያዉም አቶ ሽመልስ እንደሚሉት መድረክ የሚያደርሰዉ ጥሰትና ግድያ ሆን ተብሎ የታሰበበትና የተቀነባበረ ነዉ።

የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ መልስ-መረር-ከረር ያለም ነዉ።በግድያ የሚታወቀዉ-ኢሐአዲግ እንጂ መድረክ አይደለም የሚል።
የእስካሁኑ ዉዝግብ ወቀሳዉ ከግድያ ደርሷል።ግድያዉ በፋንታዉ ለፖለቲከኞች ሌላ መወዛገቢያ ለሕዝቡ ግን በርግጥ የሥጋት ምንጭ ሊሆን ይችላል።አቶ ቡልቻ ደመቅሳ-ፍራቸዉ የሚቀረዉ ኢሐዲግ ሲወገድ ነዉ-ይላሉ።

አቶ ሽመልስ ከማል እንደሚሉት ግን የሚያስፈራ ነገር የለም።

ምርጫዉ-አስራ ሰወስት ቀን ቀረዉ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።
Interv.Mit Shimels Kemal, Regierungssprecher
Und Bulcha Demeqssa, Oppositionen Partei

ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ