1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፥ የሥልክና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሮሮ

ረቡዕ፣ መስከረም 8 2006

«የደወሉት ቁጥር ከአግልግሎት መስጪያ ክልል ዉጪ ነዉ።» ትላለኝ አንዷ፥ «የደወሉላቸዉን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም-» ደንበኛዉ ከጎንዎ ተቀምጦ ሊሆንም ይችላል። ብቻ -The Net work is Busy Now----እያለች ትቀጥላለች፥ ሌለኛዋ።ያንኑ ቁጥር ደግመዉ ይሞክሩ----መጀመሪያ ከሰሙት የተለየ መልዕክት ይሰማሉ

https://p.dw.com/p/19k8F
Nokia mobile phones in Helsinki, Finland April 16, 2009. Nokia releases first-quarter figures on Thursday. LEHTIKUVA / Heikki Saukkomaa +++(c) dpa - Report+++
«ካገልግሎት መስጪያ---ዉጪ»ምስል picture-alliance/dpa

እዚያዉ ኢትዮጵያ፥ ከፈለጉ አሜሪካ፥ ወይም አዉሮጳ ቻይናም ይሁኑ ብቻ ወደ ኢትዮጵያ ሥልክ ይደዉሉ።ብዙ ጊዜ ከስልኩ የወዲያኛዉ መስመር የሚሰሙት ለስለስ፥ ለዘብ፥ ረጋ ያለ ድምፅ ዘና ያደርግዎት-ይሆን ይሆናል።መልዕክቱ ግን በምንም መንገድ ሊያስደስትዎ አይችልም።«የደወሉት ቁጥር ከአግልግሎት መስጪያ ክልል ዉጪ ነዉ።» ትላለኝ አንዷ፥ «የደወሉላቸዉን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም-» ደንበኛዉ ከጎንዎ ተቀምጦ ሊሆንም ይችላል። ብቻ -The Network Is Busy Now----እያለች ትቀጥላለች፥ ሌለኛዋ።ያንኑ ቁጥር ደግመዉ ይሞክሩ----መጀመሪያ ከሰሙት የተለየ መልዕክት ይሰማሉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻዉን የሚቆጣጠረዉ ኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎቱም (አንዳዶች የሌለ ነገር አገልግሎት አይባልም ይላሉ)---የባሰ ነዉ።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ አጭር ዘገባ አለዉ።

ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ