1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፤ የደሞዝ ጭማሪ ተስፋና የዋጋ ንረት

ረቡዕ፣ ሰኔ 25 2006

ሸማቾችና ተገልጋዮች እንዳሉት የደሞዝ ጭማሪዉ ገና ከንግግር ሳያልፍ ወትሮም አለቅጥ ያሻቀበዉ የሸቀጦች ዋጋ እስከ ሐምሳ በመቶ የሚደርስ አዲስ ጭማሪ ተደርጎበታል

https://p.dw.com/p/1CUcl
ምስል picture alliance/kpa

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አስተዳደራቸዉ ለመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ካስታወቁ ወዲሕ የፍጆታ ሸቀጦጭና የአገልግሎት ዋጋ እየጨመረ መሆኑን ሸማቾች አስታወቁ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ ሸማቾችና ተገልጋዮች እንዳሉት የደሞዝ ጭማሪዉ ገና ከንግግር ሳያልፍ ወትሮም አለቅጥ ያሻቀበዉ የሸቀጦች ዋጋ እስከ ሐምሳ በመቶ የሚደርስ አዲስ ጭማሪ ተደርጎበታል።ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም የደሞዝ ጭማሪ እንደሚደረግ በአንድ የበዓል መክፍቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተናገሩት ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር።ከአዲስ አበባ የደርሰን ዘገባ እነሆ።

ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ