1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራውያን ተገን  ጠያቂዎችና የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት ውሳኔ 

ዓርብ፣ የካቲት 3 2009

 «አጄንሲያ ሐበሺያ» የተባለው ስደተኞችን የሚረዳው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሥራች እና ሃላፊ ኤርትራዊው አባ ሙሴ ዘርዓይ የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት በኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ለጊዜው የከፋ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ተናገሩ ።

https://p.dw.com/p/2XMRy
Mittelmeer Rettung von Flüchtlingen
ምስል picture alliance/AP Photo/E. Morenatti

M M T/ Q&A Abba Mussie on Swiss court decision to tighten asylum criteria for E - MP3-Stereo

የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት ከአገራቸው በሕገ-ወጥ መንገድ መውጣታቸውን እንደበቂ ምክንያት በመቁጠር የኤርትራውያንን የተገን ማመልከቻ መቀበል ሊቆም ይገባል ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ባሳለፈው ውሳኔ ለቀቅ ያለው የስዊዘርላንድ የተገን አቀባበል ፖሊሲ ምክንያታዊ አይደለም ብሏል።ባለፈው ዓመት ብቻ ከ5,000 በላይ ስደተኞች በስዊዘርላንድ የተገን ማመልከቻ አቅርበው ነበር።  ከዚህ ቀደም ኤርትራውያን በስዊዘርላንድ ተገን ለማግኘት ከአገራቸው በሕገ-ወጥ መንገድ መውጣታቸውን መግለፅ ብቻ ይበቃቸው ነበር። መቀመጫውን በስዊዘርላንዷ የሴንት ጋል ከተማ ያደረገው ፌዴራል አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት አሰራሩን ከመረመረ በኋላ «ከኤርትራ በሕገ-ወጥ መንገድ መውጣት ብቻ ተገን ለማግኘት በቂ አይደለም» ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ በስዊዘርላንድ ተገን ካገኙ በኋላ ወደ ኤርትራ ለአጭር ጉብኝት የሚመላለሱ ስደተኞችን በማሳየነት ጠቅሷል። በዚህም ምክንያት በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገራቸው የወጡ ኤርትራውያን የግድ እንግልት ደርሶባቸዋል ማለት አይደለም ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። ኤርትራዊውን አባ ሙሴ ዘርዓይ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ አስተያየታቸውን ጠይቂያቸው ነበር። 

እሸቴ በቀለ 
ኂሩት መለሰ