1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ የተመድ ማዕቀብ እንዲነሳላት ጠየቀች

ሰኞ፣ የካቲት 28 2008

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ከሰባት ዓመት በፊት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ በተመድ የኤርትራ ቋሚ ተልዕኮ አምባሳደር ግርማ አስመሮም ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/1I8Y8
Girma Asmerom
ምስል AP

ምክር ቤቱ አምባሳደር ግርማ ትክክለኛ እና ኢፍትሓዊ ነው ያሉትን ማዕቀብ የጣለው ያኔ የሶማልያ ኤርትራ ተቆጣጣሪ ቡድን ኤርትራ የሶማልያን አሸባብ ቡድን ትረዳለች በሚል ያቀረበውን ምክንያት መሰረት አድርጎ እንደነበር አስታውሰዋል። ይሁንና፣ ተቆጣጣሪው ቡድን ባወጣው ዘገባው ይህንኑ ክስ የሚያረጋግጥለት ማስረጃ አለማግኘቱን እንዳስታወቀ አምባሳደር ግርማ በመግለጽ፣ ማዕቀቡ መነሳት እንደሚገባው አመልክተዋል። እንደ ጎርጎረሳዉያን አቆጣጠር ከ 2009 ዓ,ም ጀምሮ በተመድ በፀጥታዉ ምክር ቤት ተጥሎባት የነበረዉን ማዕቀብ ይነሳላት ዘንድ የጠየቀችዉ ኤትርራ በኒዮርክ በሚገኘዉ የመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ ሚሲዮን ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ግርማ አስምሮም ለፀጥታዉ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሚስተር ራፋኤል ዳሪሪ ራሜሪዝ ካሪኖ በፃፉት ደብዳቤ እንዳስታወቁት ፍታዊ ባልሆነ መልኩ በኤርትራ መንግሥት ላይ የተጣለዉ ማዕቀብ አግባብነት የሌለዉ መሆኑን ላስመዘግብ እወዳለሁ ብለዋል። ላለፉት ሰባት ዓመታት በኤርትራ ላይ ተጥሎ የቆየዉ ማዕቀብ በኃያላን ሃገራት የተቀነባበረና ሌላ ፖለቲካ አጐንዳ የያዘ ነዉ ያሉት አምባሳደር ግርማ አስምሮም የባድመ ከተማን ጨምሮ ሉዓላዊ የኤርትራን ምድር በኃይል የያዘችዉን የኢትዮጵያን ድርጊት ላለመኮነን የኤርትራን የኤኮኖሚና የወታደራዊ አቅም ለማንኳሰስና በኤርትራ የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ ማድረግን ታሳቢ በማድረግ የተጣለ ማዕቀብ ነዉ ብለዋል። መንግሥታቸዉ ለምን በዚህ ሰዓት ይሄን ደብዳቤ ለመንግሥታቱ ድርጅት ማቅረብ እንደፈለገ ለተጠየቁት ሲመልሱ «ኤርትራ ላይ የተጣለዉ ፍትሃዊ ያልሆነ ማዕቀብ መነሳት አለበት» ሲሉ ገልፀዋል።


ናትናኤል ወልዴ


አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ