1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤቦላ መከላከያ ክትባት ምርምር

ሰኞ፣ ኅዳር 22 2007

የገዳዩን የኤቦላ ተሐዋሲ የመዛመት ዜናን ተከትሎ ሰናይ ዜናን መሰማቱ ያልተለመደ ነበር። በቅርቡ ግን ተሐዋሲዉን ለመከላከል ያስችል ይሆናል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የክትባት መድሃኒት፤ ሰዎች ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጭ ዉጤትን አስገኝቶአል። ። በሌላ በኩል ክትባቱ አሉታዊ ገፆች እንዳሉትም ነዉ የተነገረዉ።

https://p.dw.com/p/1Dxlx
Symbolbild Impfung
ምስል Fotolia

ከአንድ ወር በፊት በምዕራብ አፍሪቃ የተሰራጨዉን ገዳይ የኤቦላ ተሐዋሲ በተመለከተ በዓለም የመገናኛ ብዙሃን የሚሰማዉ ዜና፤ ተሐዋሲዉን በቁጥጥር ስር ማድረግ አለመቻሉን እንደዉም ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖ የመጨረሻዉ ደረጃ ላይ መድረሱን ነበር። በምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት በከፍተኛ ፍጥነት በተዛመተዉ የኤቦላ ተሐዋሲ የተያዙ ሰዎች በአደገኛ ህመምና ስቃይ ለሞት ይዳረጋሉ። የወረርሽኙን መዛመት ለመግታት ወይም በቁጥጥር ስር ለማድረግ ከተጠበቀዉ ግዜ በላይ መዉሰዱም ይታወቃል። ይህን ተሐዋሲ ለመግታት እና ለመከላከል መፍትሄን ለማግኘት በጉጉት ላይ ያሉ ምሁራን በቅርቡ ተስፋ ሰጭ ጭላንጭልን ማየታቸዉ ተሰምቶአል። የኤቦላ ተሐዋሲን ለመከላከል እንዲያስችል ባለፈዉ መስከረም ወር በሰዎች ላይ የተደረገዉ የመጀመርያ የክትባት መከላከያ ሙከራ ዉጤትም "The New England Journal of Medicine." በተሰኘ የህክምና ድረ-ገፅ ላይ ለአንባብያን ይፋ ተደርጎአል። እንደዘገባዉ በዩኤስ አሜሪካ ሜሪላንድ ቤትሴዳ የሚገኘዉ ብሔራዊ የአለርጂ እና የኢንፊክሽን ምርምር ተቋም ከአንድ የመድሃኒት ማምረቻ ድርጅት ጋራ በመተባበር ይፋ ባደረገዉ ጥናት ፤ የኤቦላ ተሐዋሲን ለመከላከል ያስችላል የተባለ ክትባት በ20 ጤነኛ አዋቂዎች ላይ የተሞከረ ሲሆን፤ የክትባት ሙከራዉን የወሰዱት 20 ሰዎች ላይ በተደረገዉ ምርምር አመርቂ ዉጤት ማስገኘቱ ተመልክቶአል። በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ፤ ጤነኞች በሆኑ 20 በጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራ ተደርጎ ጤነኛ ወዶ ሙከራ የተደረገባቸዉ ሰዎች በ10 ሩ ላይ አነስተኛ የክትባት መጠን 10 ሩ ላይ ደግሞ በአስር እጥፍ ክትባቱን ወስደዉ፤ ከአራት ሳምንት በኋላ በታየዉ ዉጤት እንደታየዉ 20ዉም ሰዎች በደማቸዉ ዉስጥ የበሽታ ተከላከይ ሕዋሳት መገንባቱ ተጢኖአል። በጀርመን ሃንቡርግ ከተማ ላይብኒዝ ስነ -ተሐዋሲ ተቋዋም፤ ሴዛር ሙኑዝ ፎንቴላ እንደሚሉት የምርምሩ የቅድምያ ዉጤት ተስፋ ሰጭ ነዉ፤
«የመጀመሪያ ሪፖርት በመሆኑ ብዙ ማጠቃለያዎችን መስጠት አይቻልም። ቢሆንም ተስፋ ሰጪ ነገሮች አሉ። የመጀመሪያ እና ጥሩው ነገር ክትባቱ ለሰው መርዛማነት የለውም።ሪፖርቱ ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ ጥቂት ሰዎች ትኩሳት ማሳየታቸውን ይገልጻል። ቢሆንም ይህ ልንቀበለው የሚችል ነው። ያን ያህል አስከፊ ያልሆነ ትኩሳት የሚፈጥሩ ብዙ ክትባቶች አሉ።»
cAd3-EBO የሚል መጠሪያ የተሰጠዉ ይህ 20 ጤነኛ ሰዎች ላይ ሙከራ የተደረገዉ የመጀመርያ ክትባት የምርምር ዉጤት ባለፈዉ ረቡዕ ይፋ የሆነ ሲሆን ክትባቱ ከገዳዩ ከኤቮላ ተሐዋሲ መያዝ ይከላከላል ማለት እንዳልሆነም ተያይዞ ተመልክቶአል። በሃንቡርግ ስነ-ተሐዋሲ ምርምር ተቋም ምሁሩ ፎንቴላ፤ የሙከራ ክትባት ከወሰዱት 20 ሰዎች መካከል በሁለት ሰዎች ላይ ትኩሳት የታየ መሆኑንም ገልፀዋል። ለክፉ የማይሰጥ ትኩሳት በቀር የሙከራ ክትባትን በወሰዱት 20 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት ባለመታየቱ በራሱ አንድ ትልቅ ሰናይ ዜና መሆኑ ነዉ የተመለከተዉ። እንደ ምርምር ጥናቱ ዘገባ ክትባቱ በሰዉነት ዉስጥ የበሽታ መከላከያ ሕዋሳትን ይገነባል ተብሎ ይጠበቃል። የዚህ የጥናት ባልደረባ የሆኑት ሴዛር ሙኑዝ ፎንቴላ እንደሚሉት ክትባቱ በቀጣይ ኤቦላ ቫይረስ የተያዙና ከኤቦላ ተሐዋሲ ህመም ያገገሙ ላይ ክትባቱ ይሰጣል። «ይህ ሊደረግ የሚችለው ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች እና ከኢቦላ የዳኑ ሰዎች የሚያሳዩትን ምላሽ በማመዛዘን ይሆናል። በእቅዳችንም እንደዚያ ለማድረግ አስበናል።»
እንድያም ሆኖ በዚህ የጥናት ዉጤት የተገኘዉ ክትባት ከኤቦላ ተሐዋሲ ሰዎችን መታደግe መቻሉ ግን ገና እርግጠኛ እንዳልሆነ ተገልፆአል። እንደ መታደል ሆኖ አሁን ከተፈጠረው የኦቦላ ወረርሽኝ የተረፉ በርካታ ሰዎች አሉ። እነዚህ ከህመሙ መዳን የቻሉ ሰዎች ሰውነት ለበሽታው የሰጠውን ምላሽ በመሰብሰብ ከክትባቱ ጋር በማወዳደር ወደ ተሻለ ማጠቃለያ መድረስ እንደሚቻል ተገልፆአል። ተመሳሳይ አይነት ክትባት በዝያዉ በዩኤስ አሜሪካ ባልቲሞር በሚገኝ የምርምር ማዕከል ዉስጥ በሙከራ ላይ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን የምርምር ዉጤቱ በመጠናቀቅ ላይ ባለዉ የጎርጎረሳዊ ዓ,ም ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። የዚህ የሁለት ምርምር ጥምር ዉጤት አዎንታዊ ምላሽን የሚያስገኝ ከሆነ በቀጣይ የሚደረገዉ ምርምርምር ዉጤት በመጭዉ የጎርጎረሳዉያን ዓመት መጀመርያ ማለትም በሚቀጥለዉ ወር ዉስጥ እንደሚጀምር ተገልፆአል። የምርምር ስራዉ በታሰበዉ መልኩና አዎንታዊ ዉጤትን ከሰጠ ኤቦላን ለመከላከል ሰናይ ዜና ብለን መናገር እንደምንችል የወጣዉ ዘገባ ያመለክታል።

ብሪጊተ ኦስተርራት /አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

Karte Ebola Verbreitung am 10.10.2014 Englisch
Impfstoff gegen Ebola
ምስል Reuters
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ