1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤች አይ ቪ፤ ሳንባ ነቀርሳ፤ ወባና የመከላከያዉ ርዳታ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2005

ድርጅቱ የበሽታዎቹን ሥጋት ለማስወገድ የሚያደርገዉን ጥረት ለማጠናከር እና ርዳታዉን ለማስፋፋት ለሚቀጥሉት ሰወስት ዓመታት አስራ-አምስት ቢሊዮን ዶላር በሚያገኝበት ሥልት ላይ ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ከለጋሽ መንግሥታት፥ ከማሕበራትና ከድርጅት ተጠሪዎች ጋር እየተነጋገረ ነዉ

https://p.dw.com/p/18D4F
ምስል The Global Fund/Juda Mgwenya



የኤች አይ ቪ-ኤይድስ፥ የሳንባ ነቀርሳና የወባን ሥርጭትና ጉዳት ለመቀነስ የሚደረገዉ ዓለም አቀፍ ጥረት አበረታች ዉጤት ማሳየቱን በሰወስቱ በሽታዎች የተጎዱ ሰዎችን የሚረዳዉ ግሎባል ፈንድ የተሰኘዉ ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ሐላፊዎች እንደሚሉት ሰወስቱ በሽታዎች የሰዉ ልጅ አስጊ መቅሰፍት የሚሆኑበት ዘመን እያለፈ ነዉ።ድርጅቱ የበሽታዎቹን ሥጋት ለማስወገድ የሚያደርገዉን ጥረት ለማጠናከር እና ርዳታዉን ለማስፋፋት ለሚቀጥሉት ሰወስት ዓመታት አስራ-አምስት ቢሊዮን ዶላር በሚያገኝበት ሥልት ላይ ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ከለጋሽ መንግሥታት፥ ከማሕበራትና ከድርጅት ተጠሪዎች ጋር እየተነጋገረ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ