1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እህሎች ላይ የሚካሄድ ምርምር ጥንቃቄ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2007

ባለፈዉ ቅዳሜ ከ40 በላይ በሚሆኑ ሃገራት በሚገኙ 400 ገደማ ከተሞች አደባባይ የወጡ የተቃዉሞ ሰልፈኞች የምንመገበዉ በዉስጡ ምን እንዳለ የማወቅ መብት አለን፤ በእህሎች ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ከአደገኝነት ይለዩልን በማለት አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/1FWlQ
Monsanto Demonstration ANTI Gen-Soya USA
ምስል Reuters

እህሎች ላይ የሚካሄድ ምርምር ጥንቃቄ

እህሎች ላይ የሚካሄድ ምርምር ጥንቃቄ

ባለፈዉ ቅዳሜ ከ40 በላይ በሚሆኑ ሃገራት በሚገኙ 400 ገደማ ከተሞች አደባባይ የወጡ የተቃዉሞ ሰልፈኞች የምንመገበዉ በዉስጡ ምን እንዳለ የማወቅ መብት አለን፤ በእህሎች ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ከአደገኝነት ይለዩልን በማለት አመልክተዋል። ሰልፎቹ በሰሜን ደቡብ የአሜሪካን ሃገራት በተለያዩ ከተሞች፤ እንዲሁም በአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ሃገራትም ተካሂደዋል። ሞንሳንቶ የተባለዉ በዘመናዊ ቴክኒዎሎጂ የእህሎችን የተፈጥሮ ዘረመል በመለወጥ አዳዲስ የእህል ዘሮችን ለገበያ ሲል ያመርታል በሚል የተቃዉሞ ሰልፍ ሲካሄድበት በተከታታይ ዓመታት ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነዉ። የድርጅቱ ምርት የሆኑ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችም የጤና ጠንቅ መሆናቸዉን በመጥቀስ ከዚህ ቀደም በዚህ ምክንያት የጤና እክል የገጠማቸዉንና ለወደፊትም የዚህ ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ ላሏቸዉ ወገኖችም በአዉሮጳ የኅብረቱ ምክር ቤት በሚገኝበት ሽትራስቡርግ ከተማ የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት ተደርሷል። በቺሊ መዲና ሳንዲያጎ ተመሳሳይ ሰልፍ ያካሄዱ ወገኖች ደግሞ ሞሳንቶ ከሀገራቸዉ እንዲወጣ ጠይቀዋል። የብራዚሎቹ ሰልፈኞች ጭራሽ ኩባንያዉን ባዮ ቴረሪስት፤ ሲሉ አዉግዘዋል። ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ኩባንያዉ ለቀረበበት ትችት፤ ወቀሳም ሆነ እርግማን የሰጠዉ ምላሽ አለመኖሩን ነዉ።

ይህ ሁሉ ክስ የሚቀርብበት ኩባንያ የሚያካሂደዉን ምርምር የሚቃወሙ የዘርፉ ጠበብት ስጋታቸዉን በሁለት ከፍለዉ ነዉ የሚያሳዩት። አንደኛዉ የሚደረገዉ ምርምር ለጤና ጠንቅ የሚሆኑ ምርቶችን ያስከትላል፤ ሁለተኛዉ ደግሞ በምርምር የተሻሻለዉ እህል የኩባንያዉ ንብረት ሆኖ ገበሬዎች እንደወትሮዉ ሊያገኙት አይችሉም የሚል ነዉ። አልፎ ተርፎም ለሰዎች ምግብ ሊሆን የሚገበዉን እህል ለሌላ ጉዳይ እንዲዉል አመቻችቷል ተብሎም ኩባንያዉ ይወቀሳል። በዚህ ረገድ የሚያካሂደዉ ምርምርም የእህልን ምርታማነት ለማሻሻልም ሆነ ድርቅም ሆነ አረምን እንዲቋቋም ለማድረግ ከሚካሄደዉ በእጅጉ ይለያል። የድምጽ ዘገባዉን ያድምጡ፦

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ