1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 እልባት ያላገኘው የስጳኝ እና የካታላን ውዝግብ

ሰኞ፣ ጥቅምት 6 2010

የካታላን ራስ ገዝ አስተዳደር ራሱን ከስጳኝ  ለመገንጠል በሚለው ጥያቄ ላይ ከ16 ቀናት በፊት  ባካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ሰበብ ከማዕከላይ መንግሥቱ ጋር  የተፈጠረው ውዝግብ አሁን እየተባባሰ መጥቷል።

https://p.dw.com/p/2lv0g
Spanien Carles Puigdemont Premier der Regionalregierung
ምስል Reuters/I. Alvarado

አጣብቂኝ ሁኔታ ላይ የሚገኙት የካታላን መሪ

የስጳኝ ማዕከላይ መንግሥት የካታላን መሪ ካርለስ ፕዊጂዴሞንት ባለፈው ሳምንት ለምክር ቤት ባሰሙት ንግግራቸው ነፃነት አውጀው መሆን አለመሆናቸውን በግልጽ እንዲያሳውቁ የሰጣቸው ቀነ ገደብ ፕዊጂዴሞንት መልስ ሳይሰጡ ዛሬ አብቅቷል። የካታላን መሪ ካርለስ ፕዊጂዴሞንት  ዛሬ መልሳቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ እሳቸው ግን ከማዕከላዩ መንግሥት ጋር ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ንግግር እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ነው የላኩት። በዚህም የተነሳ ስጳኝ ቀነ ገደቡን እስከ ሀሙስ ማራዘሟ ተሰምቷል። ፕዊጂዴሞንት የግዛቱን ነፃነት ማወጅ አለማወጃቸውን በግልጽ ያላሳወቁበትን ምክንያት እና የስጳኝ መንግሥት በግዛቱ እና በመሪዎቹ አንጻራቸው ሊወስደው ይችላልል የሚባለውን ርምጃ በተመለከተ የብራስልሱን ወኪላችን ገበያው ንጉሤን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ኂሩት መለሰ