1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እሥራኤልና ጋዛ፣

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 2001

የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህ፣ ለፍልስጤማውያን ሰፊ የገንዘብ መዋጮ ዘመቻ እንዲካሄድ ማዘዛቸው ተገለጠ። ሳሌህ፣ በግብፅ በኩል መደኃኒትና ምግብ እንዲላክ ም አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/GR1a
የእሥራኤል አየር ኃይል በጋዛ ያደረሰው ጥቃት፣ምስል AP

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማኑቸር ሞታኪ፣ እሥራኤል ጋዛና ስትደበድብ ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምንም አላደረገም በማለት በጥባቅ ነቀፉ። የዮርዳኖስ ንጉሥ አብደላና ፍልስጤማዊቷ ባልተቤታቸው ንግሥት ራኒያ፣ በዚህ ሳምንት ከፍልስጤማውያን ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ሁለቱም ደም ሰጥተዋል። በመዲናይቱ፣ በአማን 5 ሺ የሚሆኑ ፍልስጤማውያንና ዮርዳኖሳውያን ሰላማዊ ሰልፍ ካሳዩ በኋላ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር የተሰኘው ቡድን ባሳሰበው መሠረት ጂሃድ(ቅዱስ ጦርነት) እንዲካሄድ ሲሉ መጠየቃጨው ተገልጿል። በኢስታንቡል፣ ቱርክ፣ 5 ሺ ያህል ሰዎች አደባባይ ወጥተው እሥራኤልን አውግዘዋል። ከአሥራኤል በኩል፣ ዘጋቢአችን፣ ዜናነህ መኮንን Jerusalem Post የተባለውን የእሥራኤል ጋዜጣ በመጥቀስ ከኢራን ፣ በየመንና ኤርትራ በኩል ቻይና -ሠራሽ ጦር መሣሪያ ጋዛ ገብቷል ሲል ጠቅሷል። የዜናነህ ዝርዝር ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።