1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እሥራኤል እና የአፍሪቃውያን ስደተኞች ዕጣ ፈንታ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 16 2004

አፍሪቃውያን ስደተኞች የተሻለ የኑሮ ፍለጋ እያሉ በየጊዜው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ እሥራኤል ይገባሉ። ከነዚሁ ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ ከደቡብ ሱዳን እና ከኤርትራ የሄዱ ናቸው።

https://p.dw.com/p/15KF2
Afrikanische Flüchtlinge in Israel – Viele Flüchtlinge leben in diesem Park im Süden Tel Avivs. DW/Emilie Baujard
ምስል DW

ይሁንና፡ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው ከነዚሁ ስደተኞች መካከል የብዙዎቹ ዕጣ ፈንታ በቴል አቪብ ከተማ አደባባዮች  ካለ ስራ በአስቸጋሪ ሁኔታ በእሥራኤል ህብረተሰብ ዘንድ ትልቅ ውጥረት አስከትሎዋል። ይህንን ውጥረት ለማብረድም ሲል የእሥራኤል መንግሥት ሕገ ወጦቹን ስደተኞች በጠቅላላ ከሀገሩ ለማባረር ወስኖዋል.። በዚሁ ውሳኔው መሠረትም፡ ባለፈው ሣምንት የመጀመሪያዎቹን አንድ መቶ ሀያ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ወደ ትውልድ ሀገራቸው በግዳጅ ልኮዋል።

በቴል አቪቭ ዋና አደባባይ አቅራቢያ የሚገኘው የሌቪንስኪ መናፈሻ ቦታ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ የስደተኞች መሰብቢያ ቦታ ሆኖዋእል። በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ቀኑን የሚያሳልፉት እዚያ ነው። ስደተኞቹን የመርዳት ስራ የሚያካሂደው መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ባልደረባ ኦስካር ኦሊቭየ እንዳለው፡ ቁጥራቸውም በየቀኑ እየጨመረ የሄዱት እነዚሁ ስደተኞች የሚኖሩበት ሁኔታ እጅግ አስከፊ ነው።
« አሳዛኝ ሁኔታ ነው። እጅግ ብዙዎቹ ስደተኞች ወደዚች ሀገር የገቡት በሕገ ወጥ መንገድ በመሆኑ የመታሰር ዕጣ ያጋጥማቸዋል። ከእሥር በሚለቀቁበት ጊዜ በአውቶቡስ አሳፍረው እዚህ መናፈሻ ቦታ አቅራቢያ ያመጡና ጥለዋቸው ይሄዳሉ። የሚያውቁት ሰውም ሆነ ገንዘብ የላቸውም። ይህ በመሆኑም እዚህ ይተኛሉ። »
 በትውልድ ሀገሩ ሱዳን የሚካሄደውን ውጊያ ሸሽቶ አሁን እሥራኤል የሚገኘው  ኢብራሂምም ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ መኝታውን በዚሁ መናፈሻ ቦታ አድርጓል።

« ችግሩ ፓስፖርታችን ላይ መስራት እንደማንችል ነው የተጻፈበት። ችግር ነው። እና ስራ ማግኘት አልቻልንም። ታድያ በየቀኑ እዚህ መንገድ ላይ የምቆመው ምናልባት ስራ የሚቀጥረኝ ሰው አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው። »

የእሥራኤል መንግሥት ባወጣው ይፋ መዘርዝር መሠረት፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ በሀገሪቱ ከስድሳ ሺህ የሚበልጡ ሕገ ወጥ ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ ገብተዋል። ከሱዳንና ከኤርትራ የመጡት ስደተኞች በግብፅ የሲናይ በረኃ በኩል አድርገው ነው እሥራኤል የገቡት። አንዳንዶች በጭነት ተሽከርካሪ እሥራኤል ለመግባት እስከ  3000 ዶላር እንደከፈሉ ይናገራሉ። ግን  እዚያ በሚደርሱበት ጊዜ ግን ስደተኞችን የሚቀበል አንድም ተቋም የለም፤ ይዘውት የመጡት ጊዚያዊ ቪዛም የስራ ፈቃድ አይሰጣቸውም፤ የስደተኝነቱን አቋም የሚያገኙት ደግሞ እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው። በዚህም የተነሳ ብዙዎቹ ካላንዳች ከለላ ለከፋ ችግር ይጋለጣሉ። ከአንድ ወር በፊት ቴል አቪቭ የገባውን የሀያ ስድስት ዓመቱን ኤርትራዊ መሀመድንም ያጋጠመውም ይህ ነበር።
«  ኤርትራ እያለሁ እሥራኤል በጣም ጥሩ፡ ዴሞክራሲያዊት ሀገር መሆንዋን ነበር የሰማሁት። እንደጠበቅሁት ሆና አላገኘኋትም። በጣም መጥፎ ሀገር ነው። ለስደተኛው ክብር የለም፤ ከለላ የለም፤ ስራም ሆነ ምንም ነገር የለም። ስደተኛው ሁሉ በየመንገዱ ነው የሚያድረስ። መጠለያ ቦታ አልተዘጋጀላቸውም። »
ይህ ብቻም አይደለም ስደተኞቹን የሚያጋጥመው ችግር፤ ስደተኞቹ በእሥራኤል የተስፋፋው የዘረኝነትና የውጭ ዜጋ ጥላቻም ሰለባ ሆነዋል። ከጥቂት ጊዜ በፊት በቴል አቪቭ ለተፈፀመ ወንጀል ተጠያቂዎቹ ስደተኞቹ ናቸው በሚል ህብረተሰቡ ወቀሳ ከሰነዘረና የቀኝ ክንፍ የእሥራኤል ፓርቲ አባላትም አፍሪቃውያኑን ስደተኞች ነቀርሳ እንደሆኑና ለእሥራኤልም ስጋት እንደደቀኑ ደቅነዋል በሚል ንግግር ካሰሙ  ወዲህ በእሥራኤል ህብረተሰብ እና በስደተኞቹ መካከል ውጥረቱ እየተጠናከረ መጥቶ፡ ኃይል የታከለበት ፀረ ስደተኞቹ ሁከት ተካሂዶዋል፤ አንድ ኤርትራውያን ስደተኞች የሚኖሩበትን ሕንፃም አቃጥለው አራት ስደተኞች መጎዳታቸው የሚታወስ ነው። ይህ እንደ ኦስካር ኦሊቭየ ግምት እጅግ አሳሳቢ ነው።
« በሕዝቡ ዘንድ ፍርሀትን ያስፋፋል፤ ከሕዝቡ ጋ ብዙ ዓመት ኖረናል፤ ግን አሁን የሚታየውን ዓይነት ሁኔታ አይተን አናውቅም። እና ፖለቲከኞቹ ናቸው ሆን ብለው በአፍሪቃውያኑ አንጻር ጥላቻ እንዲባባስ እያደረጉ ያሉት። የሚያስገርመው አፍሪቃውያን ያልሆኑ ወደ  200 000 የሚጠጉ የውጭ ዜጎች በእሥራኤል መኖራቸውና ስለነዚህ ሰዎች ማንም ምንም አለማለቱ ነው። ሁሉም ግን የአፍሪቃውያኑ ቁጥር  60 000  በመድረሱ ተደናግጦዋል። የህብረተሰቡ ስጋት የመነጨው አፍሪቃውያኑ በርግጥ ለሀገሪቱ አስጊ ሆነው ሳይሆን በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ብቻ  ነው ። »
የአፍሪቃውያኑን ስደተኞች ችግር በመጠኑም ቢሆን ለማቃለል አንዳንድ የሀገሬው ነዋሪዎች ከአምስት ወራት በፊት ምግብ በነፃ ማከፋፈል ጀምረዋል። በየቀኑ ለሰባት መቶ ስደተኞች ምግብ እንደሚያቀርቡ ይህንኑ የግብረ ሠናይ ፕሮዤን የጀመሩት ይጋል ስትሃይም ገልጸዋል።


« ይህ ዘረኝነት በጣም አንገፍፍፎናል። እና እንደ አንድ የሰው ፍጡር ስደተኞቹን በምችለው ሁሉ መርዳት እንዳለብኝ ይሰማኛል። እነዚህ ሰዎች ተርበዋል፤ የታመሙትም ተገቢውን ሕክምና ማግኘት አለባቸው። እኛ አሁን እዚህ ያለነው የእሥራኤል መንግሥት እና የቴል አቪቭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስደተኞቹን ለማባረር በመሞከር ላይ ስለሚገኙ ነው። »
 »
የሰኔ ወር ከገባ ወዲህ ስደተኞቹ በብዛት የሚገኙበት የሌቪንስኪ ፓርክ ሁኔታ ውጥረት ይታይበታል። የእሥራኤል ፖሊስም ወደ ሀገራቸው በግዳጅ መመለስ አለባቸው የተባሉትን ሕገ ወጥ ስደተኞችኝ፡ በየቀኑ በአማካይ ወደ ሦስት መቶዎቹን ማሰር ጀምሮዋል። የእሥራኤል መንግሥት እስካሁን የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ባለፈው እሁድ ባደረገው የመጀመሪያ በረራ ወደ ሀገራቸው መልሶዋል።
የዳርፉር ተወላጅ የሆነው አብደልአዚዝን የመሰሉ ሱዳናውያን  እና ኤርትራውያን ስደተኞች  ግን በሀገሩ ባለው አሳሳቢ ሁኔታ የተነሳ የተመድ ስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት ከለላ ስላለው ለጊዜው ከእሥራኤል ሊባረር አይችልም፤ ግን አንድ ቀን ይህ ከለላ ሊነሳና እሱም ወደ ሀገሩ ተመለስ ሊባል እንደሚችል ሰግቶዋል።
« ከየት እንደመጣሁ ሲጠይቁኝ እኖርበት የነበረው ቦታ መቃጠሉን፡ በዚያ ከነበሩት ሰዎችም መካከል ብዙዎቹ መገደላቸውን እና ብዙው ቤተሰቤም ለስደት መዳረጉን እነግራቸዋልሁ። እና ወደሀገሬ ብመለስ የት ነው የምኖረው? እኔን የመሰለ ሰው ደግሞ ሱዳን ውስጥ ተፈላጊ አይደለም። አንዴ ወደ እሥራኤል መጥተናል፤ ብንመለስ መታሰር ወይም መገደል ነው የሚጠብቀን። »
የእሥራኤል መንግሥት  ሊመልሳቸው ለማይችለው ስደተኞች በነጌቭ በረኃ ወደ 12 000 የሚጠጉ ስደተኞችን የሚይዝ መጠለያ ማዕከል ገንብቶዋል።  

አርያም ተክሌ
ኤሚሊ ቦዣር
መሥፍን መኮንን

South Sudanese on board a bus wave the national flag as they drive from the bus terminal in Tel Aviv, Israel, Sunday, June 17, 2012 to Ben Gurion airport to leave for South Sudan. Israel is forcing 120 South Sudanese to leave the country as authorities try to whittle the number of illegal immigrants. Interior Ministry spokeswoman Sabine Haddad says all 120, who are being flown out on Sunday, agreed to leave voluntarily. She says they were told they faced arrest if they did not sign a form agreeing to leave. She says adults will receive 1,000 euros ($1,300) and minors 500 euros ($650) per person. (Foto:Ariel Schalit/AP/dapd)
ምስል AP
African refugees share breakfast at a shelter in Tel Aviv, Israel Thursday, Feb. 16, 2012. Some 50,000 Africans have entered Israel in recent years, fleeing conflict and poverty in search of safety and opportunity in the relatively prosperous Jewish state. A growing number of African migrants say they were captured, held hostage and tortured by Egyptian smugglers hired to sneak them into Israel.(Foto:Oded Balilty/AP/dapd)
ምስል AP
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ