1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤልና በፍልስጤማውያን ግዛት የቀጠለችው የሰፈራ ግንባታዋ

ማክሰኞ፣ መስከረም 26 2002

እስራኤል በያዘችው የምዕራባዊ ዳርቻ የሰፈራ ቦታ ግንባታዋን ቀጠለች።

https://p.dw.com/p/K043
የሰፈራ ቦታ በኢየሩሳሌምምስል AP

«ሰላም አሁን» የሚባለው ድርጅት ባወጣው ዘገባ መሰረት፡ ምንም እንኳን እሥራኤል፣ ግንባታውን እንድታቋርጥ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፡ በተለይ ከዩኤስ አሜሪካ ተጽዕኖ ቢያርፍባትም ይህን ችላ በማለት ስምንት መቶ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ትገኛለች። ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በሰላሳ አራት ቦታዎች የሰፈራ ግንባታው ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል። ይህም በፍልስጤማውያን እና በእስራኤል መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት እንዳያደናቅፍ እጅግ ነው ያሠጋው።

ዜናነህ መኮንን/አርያም ተክሌ/ተክሌ የኋላ