1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ርምጃ ኤርትራውያን ስደተኞችን ይመለከታል

ማክሰኞ፣ ኅዳር 12 2010

የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ 40,000 አፍሪቃውያን ተገን ጠያቂዎችን ከሀገራቸው ለማስወጣት ዓለም አቀፍ ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ከትናንት በስቲያ እሁድ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለስምምነቱ ዝርዝር ነገር ባይናገሩም "እጅጉን ጠቃሚ ነው" ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2o18H
Israel Flüchtlinge in Holot Haftanstalt
ምስል Getty Images/AFP/M. Kahana

የእስራኤል ርምጃ በዋናነት ኤርትራውያን ስደተኞችን ይመለከታል

ከእስራኤል የሚባረሩት ተገን ፈላጊዎች ያለፈቃዳቸው እንደሆነ በዘገባዎች ተገልጿል። ከጎርጎሮሳዊው 2000 የመጀመሪያ አመታት ጀምሪሮ ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን በግብፅ በኩል ወደ እስራኤል ቢገቡም በሀገሪቱ ግን ተቀባይነት አላገኙም። ስደተኞቹ በእስራኤላውያን ዘንድ "ሰርጎ ገቦች" የሚል ስም እንደተሰጣቸው ዘገባዎች አመልክተዋል።  ሐሬትዝ የተባለው የእስራኤል ዕለታዊ ጋዜጣ ኔታንያሁ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ስምምነት ደርሰዋል ሲል ባለፈው ወር ዘግቦ ነበር። እየሩሳሌም ከሚገኘው ዘጋቢያችን ዜናነህ መኮንን ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ዜናነህ መኮንን

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ