1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«እንቡጥ» የኢትዮ - ፈረንሳይ መርጃ ማኅበር

ሰኞ፣ ኅዳር 8 2007

ኢትዮጵያዊዉና ፈረንሳዊት ባለቤታቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመማርያ ቁሳቁስ ለሌላቸዉ ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ከ 22 ዓመታት በፊት የጀመሩት የርዳታ ግልጋሎት ቆየት ብሎ ይህን ዓላማ የደገፉ ኢትዮጵያዉያንና ፈረንሳዉያን አካቶ «እንቡጥ» በተሰኘ የርዳታ ማኅበርነት መቋቋሙ ተመልክቶአል ።

https://p.dw.com/p/1DolS
Embut Äthiopien
ምስል Haimanot Turuneh

በጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓ,ም ፈረንሳይ ዉስጥ ህጋዊ ሆኖ ተመስርቶ ችግረኛ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎችን ከፍተኛ እገዛ እየሰጠም ነዉ። ማኅበሩ በተለይ አዲስ አበባ ሾላ አካባቢ በሚገኘዉ «አድዋ በር» የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸዉ ቤተሰቦች የመጡ ተማሪዎችን፤ ወላጆቻቸዉን በሞት የተነጠቁ ችግረኛ ልጆችን እንዲሁም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን እንደሚረዳ ታዉቋል። እነዚህ ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን እስኪያጠናቅቁ ድረስ መማሪያ ቁሳቁስ በመስጠት ለተወሰኑ ተማሪዎች ደግሞ የኪስ ገንዘብ ሁሉ በመስጠት ድጋፍ ያደርጋል። የርዳታ ማኅበሩ ችግረኛ ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን የሚረዳዉ፣ በተጨማሪ ለትምርት ቤቱ የመማርያ ቁሳቁሶችን ይሰጣል።

ሐይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ