1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦባማና በአፍሪቃ ላይ ይከተሉታል ተብሎ የሚጠበቀው መርሀቸው

ማክሰኞ፣ ጥር 19 2001

የመጀመሪያው አፍሪቃ አሜሪካዊው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ቃለ መሀላ ከፈፀሙና ፕሬዝዳንታዊ ስራቸውን ማካሄድ ከጀመሩ እነሆ ዛሬ ሳምንታቸውን ደፈኑ ።

https://p.dw.com/p/GhS4
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማምስል AP

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የገቡዋቸውን ቃሎችም ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል ። ዓለም ከርሳቸው ብዙ የሚጠብቀው ኦባማ የሀገራቸው የውጭ ፖሊሲ ተቀባይነት እንዲያገኝ እየጣሩ ነው ። በሌላም በኩል አያሌ አፍሪቃዊ የኦባማ ዕርምጃና አቋም ብዙ ለውጥ ያመጣልናል ብሎ በመጠበቅ ላይ ይገኛል ። ለመሆኑ ኦባማ በአፍሪቃ ላይ የሚወስዱት የአቋም ለውጥ ምን ይሆን ? የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ይህን መነሻ አድርጎ የአንድ የብሪታኒያ የጥናት ተቋም ተመራማሪን አነጋግሯል ።

ኦባማና በአፍሪቃ ላይ ይከተሉታል ተብሎ የሚጠበቀው መርሀቸው