1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አድማ፤ ሦስተኛ ቀን

ረቡዕ፣ የካቲት 28 2010

 ብዙዎች የተቃወሙት አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈዉ አርብ የፀደቀበት መንገድ ደግሞ ሌላ ጥርጣሬ፤ የሕጋዊነት ጥያቄ እና ተቃዉሞ ገጥሞታል።የኦሮሞ ፌደራሊስት ጎንግረስ (ኦፌኮ) አዋጁን በጋዜጣዊ መግለጫ ከመቃወም አልፎ መንግሥትን በሕግ ለመሞገት ወስኗል

https://p.dw.com/p/2ttTW
Äthiopien Proteste | Ambo Town
ምስል DW/M. Yonas Bula

NM - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈዉ አርብ ያፀደቀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተመታዉ የስራ ማቆም አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ነዋሪዎች እና ፖለቲከኞች አንደገለፁት በየከተሞቹ የንግድ ተቋማት እና መንገዶች ዛሬም ተዘግተዉ ነዉ ያረፈዱት።ካለፈዉ ዓረብ እስከ ሰኞ ድረስ የቀጠለዉ ግጭት እና ግድያ ግን ዛሬ ጋብ ብሎ ማርፈዱ ተነግሯል።ተቃዋሚዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በበኩሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፀደቀበት ወቅት እና መንገድ ሕገ-ወጥ ነዉ በማለት  መንግሥትን ለመክሰስ ወስኗል።

እስከትናንት በቀጠለዉ ግጭት የሞተ-የቆሰለዉን ሰዉ ቁጥር በትክክል የሚያዉቅ እስካሁን የለም።የሟቹን ቁጥር አንዳዶች አምስት፤ ሌሎች ከአስር በላይ ይሉታል።የተቃዋሚዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ምክትል  ፕሬዝደንት አቶ ሙላቱ ገመቹ ሰዉ የሞተባቸዉን አካባቢዎች በከፊል ይጠቅሳሉ።

                             

Äthiopien Proteste | Mulatu Gamachu
ምስል DW/M. Yonas Bula

 

ያዩ እንደሚሉት ግጭት ግድያዉ ጋብ በማለቱ ነዋሪዎች  ሙታቸዉን ለመቅበር፤ ሐዘን ለመቀመጥ፤ ቁስለኛ ለማስታመም ፋታ አግኝተዋል። ምክንያቱ ግን አነጋጋሪ ነዉ። ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ለሰወስት ቀን የተጠራዉ አድማ ግን ነዉ።                             

ለሁለተኛ ጊዜ የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳይፀና የተለያዩ ወገኖች ሲጠይቁ ነበር።ዩናይትድ ስቴትስ፤ የአዉሮጳ ሕብረት እና ብሪታንያ አዋጁን ተቃዉመዉታል።ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ድርጅቶች እና የሕግ ባለሙያዎች አዋጁ የሐገሪቱን ሕገ-መንግሥት ይፀረራል በማለት ተችተዉታል።የተቀበላቸዉ የለም።

 ብዙዎች የተቃወሙት አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈዉ አርብ የፀደቀበት መንገድ ደግሞ ሌላ ጥርጣሬ፤ የሕጋዊነት ጥያቄ እና ተቃዉሞ ገጥሞታል።የኦሮሞ ፌደራሊስት ጎንግረስ (ኦፌኮ) አዋጁን በጋዜጣዊ መግለጫ ከመቃወም አልፎ መንግሥትን በሕግ ለመሞገት ወስኗል።የፓርቲዉ ምክትል ፕሬዝደንት ሙላቱ ገመቹ እንደሚሉት ፓርቲያቸዉ መንግሥትን የሚከስበት በቂ ምክንያት አለዉ።ምክንያት አንድ። በዚሕ ወቅት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስደነግግ ምንም ምክንያት የለም።                                             

የሕግ ባለሙያ ወንድሙ ኢብሳ ደግሞ  ሕገ-መንግሥቱን የሚፃረር የሚል ሕጋዊ ምክንያት ያክሉበታል።                                       

የኦፌኮ ምክትል ፕሬዝደንት እንደሚሉት ፓርቲያቸዉ መንግስትን ከስሶ መንግሥት ከሚቆጣጠረዉ ፍርድ ቤት ፍትሕ አገኛለሁ የሚል እምነት የለዉም።ይሁንና መንግስት የራሱን ሕግ የሚጥስ መሆኑ መጋለጥ አለበት፤-አቶ ሙላቱ እንደሚሉት።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ