ከሊቢያ ለጉዞ የተዘጋጁ ስደተኞች
ዓርብ፣ ጥቅምት 1 2006ማስታወቂያ
እንደተናገሩትም በሱዳን በኩል ኣድርገው ሊቢያ እስኪደርሱ በዚህ ረጅም የበረሃ ጉዞ የደረሰባቸውስቃይ ሳያንሳቸው ኣሁንም የባህር ላይ ኣሰቃቂ ጉዞ ይጠብቃቸዋል። በእርግጥ ስደተኞቹ እንደሚሉት ያ ከሁለት መጥፎ ይሻላል ብለው የመረጡት የተሻለ መጥፎ በመሆኑ እዚያው ሊቢያ ውስጥ በፖሊሶች የሚደርስባቸውን ዘረፋ እና እስራት ነው ይበልጥ የሚያማርሩት።
ከ UNHCRየጀኔቫ ቢሮ ቃል ኣቀባዩ ሚ/ር ዳን ሚክኖኣፓኔ እንደሚሉት ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት የሚደረገው ጥረት ማነጣጠር ያለበት መነሻው ላይ ነው።
ይህ ግን ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ ሚ/ር ዳን እንደሚሉት የኣውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ስደተኞች ተገን የሚጠይቁበትን ቦታ እና የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደገና ሊመረምሩ ይገባል። ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ የባህር ላይ ቁጥጥሩም በእርግጥ ሊጠናከር ይገባል ባይ ናቸው ሚ/ር ዳን።
ጃፈር ዓሊ
ሸዋዬ ለገሰ