1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሳዉዲ የኢትዮጵያዉያን አቤቱታ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 24 2006

የሳዉዲ መንግስት የሰጠዉ የምህረት አዋጅ የጊዜ ገደብ ካለቀ በኋላ በሪያድ መንፉአ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ከደረሰ ወዲህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸዉም ሆነ ካመጣቸዉ አሠሪ ጋ የማይሠሩ ማናቸዉም ዜጎች እንደህገወጥ እንደሚቆጠሩ በማሳሰብ፤

https://p.dw.com/p/1AkYo
ምስል AFP/Getty Images

ሳዉድ አረቢያን ለቀዉ እንዲወጡ የኤምባሲና ቆንስ መስሪያ ቤቶች ተደጋጋሚ ማስታወቂያዎች ማዉጣታቸዉ ይታወሳል። ይህን ጥሪ ተከትሎም በአብዛኛዉ በሃጂና በዑምራ እንዲሁም በባህር ወደሳዉዲ የገቡ ከ150 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵዉያን ሀገሪቱን ለቀዉ የወጡ ቢሆንም ካመጧቸዉ አሰሪዎች ጋ ባለመስራታቸዉ ህገወጥ የተባሉት ኢትዮጵያዉያን ወደሀገር ግቡ ለሚለዉ ጥሪ የሰጡት ምላሽ ግን ቀዝቀዝ ያለ እንደነበረ ነዉ የጂዳዉ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ በላከዉ ዘገባ ያመለከተዉ። ካለፈዉ ሳምንት አንስት ተጠናክሮ የቀጠዉ አሰሳ ያሰጋቸዉና እንመለሳለን ብለዉ ሲዘጋጁ ወገኖች ደግሞ ያልጠበቁት ሌላ ችግር እንደገጠማቸዉ ይናገራሉ።

ነቢዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ