1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከባሬስታነት እስከ ታዋቂ ተዋናይነት

እሑድ፣ የካቲት 4 2010

ገብርዬን ሆኖ ያለምንም ልምምድ ለመጀመርያ ጊዜ በመድረክ ላይ የቀረበዉ የዝያን ጊዜዉ ጀማሪ ተዋናይ ሱራፌል፤ የባሕርዳር የአማራ ክልል የባህልና የዘመናዊ ትያትር ቡድን ሲቋቋም ተወዳድሮ አሸንፎ ወደ ተዉኔት ጉዞዉን ጀመረ። በባህርዳሩ የትያትር ቡድን ዉስጥ በተለይ የአፄ ቴዎድሮስን ገፀ-ባህሪ ተላብሶ ለረጅም ዓመት አገልግሎአል።

https://p.dw.com/p/2sSr8
Artist Surafel Teka  & Getenat eneyew on Europe Tour
ምስል Surafel Teka

ተዋናይ ሱራፌል ተካ

በጎንደር እንብርት ፒያሳ ተወልዶ፤ የአንገበርን ዉኋ ጠጥቶ፤ ጃንተከል ዋርካ ዙርያ ተዝናንቶና ቦርቆ ያደገዉ፤ ተዋናይ ፋሲል ተካ በልጅነቱ ከሊስትሮነት ሎተሪ አዟሪነት ሥራን ጀመረ። በመለጠቅ በዝያዉ በከተማዋ ሲማቤት ቡና ቤት ዉስጥ በአስተናጋጅነት ተቀጥሮ ሲሰራም ለዛሬዉ የመድረክ ፈርጥነት መብቃቱን እሱ ብቻ ሳይሆን አድናቂዎቹ አብሮ አደጎቹ ይመሰክራሉ። በጎንደር ሲኒማ ቤት የጀመረዉ የመድረክ ተዉኔት ባሕርዳርን ይዞ በቀጣይ መዲና አዲስ አበባ ላይ በተለይ የቋራዉን ጀግና የአፄ ቴዮድሮስን ጀግንነት ገፀ  ባሕሪና አልባሳቱን ተላብሶ ሲተዉን ተወዳጅነት እና ታዋቂነትን አትርፎለታል። ይኸዉ ድንቅ ትዉናዉ በሰሜን አሜሪካ ከ 25 ብላይ ግዛቶች ተዘዋዉሮ እንዲጎበኝ ድንቅ ትርዔቱን ለተመልካቹ እንዲያቀርብ በርከፍቶለታል። በሰሜን አሜሪካ ብቻ ሳይሆን በመኃል አዉሮጳ ሐገራትም የተለያዩ ሐገራትን በተለይ ደግሞ መዲና ጀርመንን ተዘዋዉሮ ጎብኝቶአል። ተዋናይ ሱራፌል ተካ በጀርመን ቆይታዉ ዶይቼ ቬለን ለማግኘት እድል ባያገኝም ዛሬ ከሚገኝበት አዲስ አበባ ከሚተዉንበት ከመድረክ ጀርባ በሥልክ አግኝተን በእንግድነት ይዘነዋል።

Artist Surafel Teka  & Getenat eneyew on Europe Tour
ምስል Surafel Teka

የዛሬዉ የመድረክ ተዋናይ ሱራፌል ተካ በልጅነቱ የፊልምን ማየት ስለሚሻ ብቻ ሲኒማ ቤት ተቀጥሮ በብዛት ፊልምን ለማየት እንደበቃ እና ከተመለከተዉ ፊልም በኋላ የተማረከበትን የፊልም አክተር ገፀ-ባህሪን አስመስሎ መጫወት መጀመሩ ለዛሬዉ የትያትር መድረክ ትወና ጥርግያ እንደከፈተለት ይናገራል።

ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

አዜብ ታደሰ