1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከተሜ ወጣቶችና አለባበሳቸው

ዓርብ፣ ግንቦት 19 2003

በአንዳንድ በኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ከምዕራቡ ዓለም የወሰዱት አለባበስ፤ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ መኖሩን አንዲት የማህበረሳብ ባለሙያ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/RQ8A
ምስል dpa

« ለምሳሌ ሴቶች በአብዛኛው ሱሪ ሲለብሱ፤ የሰውነት ቅርፃቸውን በሙሉ በሚያሳይ መልኩ ለብሰው ሲንቀሳቀሱ ይታያል። ይህ ባህላችን አይደለም።»ይላሉ ወ/ሮ ሂሩት ዮሴፍ። Forum on Sustainable Child Empowerment በተባለ አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ያገለግላሉ። የማህበረሳብ ጉዳይ ባለሙያ ናቸው። ድርጅታቸው በተለይም የጎዳና ተዳዳሪዎች፤በመረጡት፣ የሙያ መስክ የሚሰለጥኑበትን ሁኔታ በማመቻቸት፤ በመልሶ ማቋቋሙ ላይ ያተኩራል። የማህበረሳብ ባለሙያዋ፤ በመስራቤታቸው ስላላቸው የሙያ ድርሻ ሳይሆን፤ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በከተማው አካባቢ ስላለው አለባበስ፤ ያላቸውን ተሞክሮ አካፍለውናል። የአንዳንድ የኢትዮጵያ ከተሞች ወጣቶች አለባበስ ከጊዜ ወደ ጊዜ አጠያያቂ በሆነ ሁኔታ ተቀይሯል። ዘመናዊ ከምዕራቡ አለም የሚመጡ አለባበሶች በከተሞቹ ዘንድ ምን አይነት ሚና እየተጫወቱ እንደሆነና በምን አይነት መልኩ፤ ወጣቶቹ የአገራቸውን ባህል በማይጎዳ መልኩ ሊያዛምዱት ይችላሉ። እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮች በባህል ዝግጅቱ ላይ ተነስተዋል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ