1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኢትዮጵያ የተለቀቁት ጋዜጠኞች መግለጫ

ዓርብ፣ መስከረም 4 2005

ጋዜጠኞቹ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተይዞባቸዉ የነበረዉን የወንጀል ጭብጥ በሙሉ ክደዋል።ይቅርታ የጠየቁትም እነሱ እንደሚሉት ተገድደዉ ነዉ

https://p.dw.com/p/169Nu
Schweden Flagge

ኢትዮጵያ ዉስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ጥሶ በመግባትና ከአሸባሪዎች ጋር በመተባበር ወንጀል እያንዳዳቸዉ አስራ-አንድ ዓመት እስራት ተበይኖባቸዉ ባለፈዉ ሰኞ በይቅርታ የተለቀቁት ሁለት የሲዊድን ጋዜጠኞች ያስፈረደባቸዉን ወንጀል አልፈፀምን አሉ።ጋዜጠኞቹ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተይዞባቸዉ የነበረዉን የወንጀል ጭብጥ በሙሉ ክደዋል።ይቅርታ የጠየቁትም እነሱ እንደሚሉት ተገድደዉ ነዉ።ጋዜጠኞቹ የሰጡትን መግለጫና የተደረገላቸዉን አቀባበል የተከታተለዉን የስቶክሆልሙን ዘጋቢያችን ቴዎድሮስ መራሕቱን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ጋዜጠኞቹ ምን አሉ የሚል ነበር።ከመልሱ እንጀምር፣-

ቴዎድሮስ መብራቱ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ