1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከዳ ኑሙ

ረቡዕ፣ ሰኔ 23 2002

በዚሕም ምክንያት ቅሬተ-አፅሙን ያገኙት ሳይንቲስቶች አፅሙ በተገኘበት አካባቢ ሕዝብ በአፋር ቋንቋ ከዳ ኑሙ ብለዉታል

https://p.dw.com/p/O79e
ሉሲ-ቅም አያት ተገኘምስል AP

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከ3.6 ሚሊዮን በላይ እድሜ እንዳለዉ የሚገመት የጥንተ-ሠዉ ቅሬተ አፅም በርቅቡ ተገኝቷል።ይሕ የጥንታዊዉ የሰዉ ዝርያ የወንድ ቅሬተ-አፅም ከዚሕ ቀደም ከተገኘችዉ ከዝነኛዋ ከሉሲ በአራት መቶ ሺሕ አመት ግድም የሚበልጥ ነዉ።በቁመትም ሉሲን ይበልጣል።በዚሕም ምክንያት ቅሬተ-አፅሙን ያገኙት ሳይንቲስቶች አፅሙ በተገኘበት አካባቢ ሕዝብ በአፋር ቋንቋ ከዳ ኑሙ ብለዉታል።ከዳ ኑሙ ትልቁ ሰዉ ማለት ነዉ።የዛሬዉ የሳንስና ሕብረተሰብ ዝግጅት ይንን የሚመለከት ነዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ አዘጋጅቶታል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ