ከድንበር የተጠለፉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ
ሐሙስ፣ ግንቦት 9 2004
የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በኤርትራ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ለማስለቀቅ ሙከራውን መቀጠሉን አስታወቀ ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ዛሬ እንዳሉት መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ጥረቱን አላቋረጠም ። የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ክሱን አስተባብሏል ። የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ፀሃዬ ፋሲል የኢትዮጵያ ውንጀላ የተለመደና ፣ መንግሥት ውስጣዊ ችግሮቹ ላይ እንዳይተኮር የሚጠቀምበት ዘዴ ነው ሲሉ ተናግረዋል ። ሁለቱንም ያነጋገረችው ሂሩት መለሰ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች
የኢትዮጵያ መንግሥት ጎረቤት ኤርትራ ዜጎቼን አፍና ወስዳለች ሲል በይፋ ከከሰሰ አንድ ወር አልፏል ። የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አንዳንድ ነዋሪዎችና አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ፣ ከአካባቢው ወጣቶች መጠለፋቸው ከተነገረበት ከዚያን ጊዜ ወዲህም አፈናው መቀጠሉን ይናገራሉ። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ የተጠለፉት ሰዎች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከተገለፀው የተለየ እንዳልሆነ ነው ያስረዱት
ኤርትራ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ክድንበር አካባቢ አፍና ወሰደች መባሉን ግን ሃሰት ስትል ነው ያስተባበለችው ። የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ፀሃዮ ፋሲል
ኢትዮጰያ አፈናው በኤርትራ መንግሥት ለመከናወኑ መረጃ አለኝ ትላለች ።
የኤርትራ መንግሥት ወጣቶቹን ስለማፈኑ ኢትዮጵያ የምታቀርበው ማስረጃ ምንድነው ተበለው አቶ ዲና ለተጠየቁት ሲመልሱ
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፀሃዮ እንደሚሉት ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ይህን መሰሉ ክስ ሲሰነዘር አዲስ አይደለም ። ኢትዮጵያ ይህን የምታደርገውም በርሳቸው አባባል የውስጥ ችግሮችዋን ወደ ሌላ ወገን ለማላከክ ነው ።
ኤርትራ ይህን ስትል የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ የተያዙትን ዜጎች ለማሰለቀቅ 3 አብይ ስልቶችን እየተከተልኩት ነው ይላል ። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
አቶ ፀሃዮ ፋሲል ግን ምንም በሌለበት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሊኖር አይችልም ነው የሚሉት
ድምፅ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ