1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፍተኛ የበቆሎ ምርት ዉጤት በደቡብ አፍሪቃ 

ረቡዕ፣ ሰኔ 21 2009

ደቡብ አፍሪቃ በ 36 ዓመት ታሪኳ ከፍተኛ የተባለዉን የበቆሎ ምርት ማግኘትዋን አስታወቀች።  ኢሊኒኞ የተባለዉ የተፈጥሮ ክስተት በሚያስከትለው የአየር መዛባት  ባመጣዉ የአየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት ድርቅእና የሰብል እጥረት  አጋጥሟታል።

https://p.dw.com/p/2fUGe
A handful of maize seed
ምስል CC /Anne Wangalachi/ CIMMYT

Ber.Joburg (Südafrika_die größte Maize Ernte in 36 Jahren+) - MP3-Stereo

በወቅቱም ደቡብ አፍሪቃ ከተለያዩ ሃገራት የበቆሎ ምርትን መግዛትዋ ይታወቃል። ከፍተኛ የበቆሎ አምራችና ተጠቃሚ መሆንዋ የሚነገርላት ደቡብ አፍሪቃ የደረሰባትን የምግብ እጥር ችግር ለመቅረፍ ባደረገችዉ ትግል ታሪኳን መቀየርዋ ተሳክቶላታል። የገጸ- ምድርም ሆነ የከርሰ ምድር ዉኃ ሐብት ባለቤት የሆነችዉ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪቃ ትምህርት መቅሰም እንደምትችል የግብርና ባለሙያዎች ጠቁመዋል። ከጆሃንስበርግ  ወኪላችን መላኩ አየለ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።   


መላኩ አየለ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ