1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ 10 ዓመት ወዲህ የረሃብ ይዞታ በዓለም ዙሪያ፧

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 21 1999

ከአሥር ዓመት በፊት፧ የዓለም መሪዎች፧ ሮማ ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ፧ ረሃብንም ሆነ ድኅነትን እ ጎ አ እስከ 2015 ዓ ም ግማሽ በግማሽ ለመቀነስ ቃል መግባታቸው ይታወስ ይሆናል።

https://p.dw.com/p/E0dO
ረሃብ በኬንያ፧
ረሃብ በኬንያ፧ምስል AP

የጀርመን የልማት ጉዳይ ድርጅቶች፧ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፧ ድኅነርን በመታገል ረገድ፧ የሚገባውን አላከናወነም በማለት ወቅሰዋል። የተባባሩት መንግሥታት የምግብና ግብርና ድርጅት(FAO) ከጀርመናውያን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፧ German Watch, Brot für die Welt, Misereor እንዲሁም FIAN በሚል ምኅጻር ከታወቀው የሰብአዊ መብት ድርጅት ጋር እስከ ፊታችን ቅዳሜ የሚዘልቅ «የተፈጥሮ አካባቢና ልማት« በሚል መሪ ርእስ የተዘጋጀ ውይይት በማካሄድ ላይ ነው። አጥጋቢ ሆኖ ስላልተገኘው ያለፉት አሥር ዓመታት ጥረት Sabine Ripperger ያቀረበችውን ሐተታ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው ሰብስቦታል።
የዓለም መሪዎች፧ የምግብን እጥረት አስመልክተው ከመከሩ ከአሥር ዓመት ወዲህም ቢሆን፧ በዓለም ዙሪያ አሁንም 854 ሚልዮን ህዝብ፧ በረሃብ በመማቀቅ ላይ እንደሚገኝ ነው የሚታወቀው። እ ጎ አ እስከ 2015 ዓ ም ድኅነት ግማሽ በግማሽ እንዲቀነስ ይደረጋል መባሉ ህልም ነው። (እንጀራ ወይም ዳቦ ለዓለም) Brot für die Welt የተሰኘው የጀርመን ወንጌላውያን የግብረ ሰናይ ድርጅት ባልደረባ፧ Bernhard Walter ረሃብን ለማስወገድ በመታገሉ ረገድ እመርታ የሚታየው በቻይናና ህንድ ይሆናል ባይ ናቸው። ረሃብ የሚያጠቃው በአማዛኙ በተወሰነ አካባቢ የሚኖረውን የኅብረተሰብ ከፊል ነው።
1. O-Ton Walter, dt.
“80 ከመቶው ረሃብቶች የሚገኙት፧ በገጠር ነው። በይበልጥ የሚራቡት፧ በግብርና ተሠማርተው የዕለት ጉርሳቸውን የሚያገኙት ወገኖች ናቸው። ከእነዚህም መካከል፧ ሃምሳ ከመቶው፧ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው በተለይ ኻያ ሁለት ከመቶው መሬት የሌላቸው ሆኖም በገጠር የሚኖሩ የእርሻ ሠራተኞችና የተግባረ ዕድ ባለሙያዎች ናቸው። ስምንት ከመቶው ደግሞ፧ ከተፈጥሮ ሀብት የዕለት ጉርሳቸውን የሚያገኙ አሣ አጥማጆች፧ እረኞችና አርብቶ አደሮች ናቸው።«
ከ German Watch ቶቢያስ Reichert የተባሉት በበኩላቸው፧ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት አገሮች፧ ማንኛውንም ምርት ወደ አዳጊ አገሮች በመላክ፧ ገበያውን ያሰናክላሉ ብለዋል። ከ Brot für die Welt በርንሃርት ቫልተር እንደገለጹት፧ በአሁኑ ወቅት በልማት ኋላ-ቀርነት ሳቢያ አሳሳቢ የሆኑት አፍሪቃ ውስጥ፧ ከሰሃራ ምድረበዳ በስተደቡብ የሚገኙት አገሮች ናቸው።

2. O-Ton Walter, dt.
«ጋናና ሞዛምቢክ በልዩ ዓይን የሚታዩ ናቸው። የሚያስደንቀው በእርስ-በርስ ጦርነት አያሌ ዓመታት የተዳቀቀችው ሞዛምቢክ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገግማ እመርታ ማሳየቷ ነው። እርግጥ ጋናም፧ እ ጎ አ 1980 ኛዎቹ ዓመታት በመጥፎ ሁኔታ ላይ እንደነበረች የሚዘነጋ አይደለም። አሁን በጋና የሠመረ እርምጃ ነው የሚታየው። ነገር ግን ባጠቃላይ የአፍሪቃ ይዞታ ብሩኅ ሁኔታ የሚንጸባረቅበት አይደለም።«
በዛ ያሉ ረሃብተኞች የሚገኙት በንዑሱ ክፍለ ዓለም በህንድ ነው። ብዛታቸው 220 ሚልዮን ነው። ህንድ በአንድ በኩል፧ ስንዴ፧ ለዓለም ገበያ ታቀርባለች። በሌላ በኩል ብዙው ህዝቧ በቂ ምግብ ለመግዛት ገንዘቡ የለውም«።
FIAN የተሰኘው ምግብ ማግኘት መሠረታዊ መብት ነው ብሎ የሚንቀሰቀሰው የሰብአዊ መብት ድርጅት፧ ባልደረባ አርሚን ፓሽ፧ ቻይናና ህንድ አዎንታዊ ግሥጋሴ እንደሚያደርጉ ይገልጻሉ።
3. O- Ton Paasch, dt.
«በቻይና በከፊልም በህንድ፧ በተለይ በኬራላ ሰፊ የመሬት ማከፋፈያ እርምጃ፧ ደረጃ በደረጃ ተፈጻሚነትን አግኝቷል። በልማት ጠበብት ረገድ፧ የመሬት ይዞታን የሚመለከት የተሃድሶ ለውጥ እንዲሁም በዚሁ የኤኮኖሚ ዘርፍ ገንዘብን ሥራ ላይ ማዋሉ፧ ወሳኝነት አለው። ብድር፧ ድጎማ፧ አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ፧ የመሠረተ ልማት መዋቅር፧ ትኩረት ተደርጎባቸዋል። የግብርናው ዘርፍ እንዲነቃቃ፧ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ-አደሮችም እንዲበረታቱ ተደርጓል። ወሳኝነት ያለው እርምጃም ሆነ ድርሻም ይኸው ነው። «
የልማት ድርጅቶቹ፧ የጀርመን ፌደራል መንግሥት፧ ረሃብን በመታገል ረገድ ዳተኛነትን አሳይቷል በማለት ተችተዋል። እርግጥ ነው ጀርመን፧ በዓለም አቀፍ መድረክ፧ ምግብ የማግኘትን መብት ለማስከበር ጠቃሚ ድርሻ አበርክታለች። የልማት ተራድዖ ሚንስትር ወይዘሮ ሃይደማሪ ቪቾሬክ Zeul ወቀሳው አግባብነት የለውም ይላሉ። እርሳቸው የሚመሩት ሚንስቴር፧ በ 30 አገሮች በገጠር ልማት እንዲፋጠን በአጠቃላይ 300 ሚልዮን ዩውሮ መመደቡንም አያይዘው ገልጸዋል።