1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ40 ዓመት በፊት በ60 ሹማማንት ላይ የተፈጸመ አስደንጋጭ ድርጊት

ሰኞ፣ ኅዳር 15 2007

«ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም» የሚል መዝሙር እየዘመረ ፣ አዝጋሚ የተሰኘውን አብዮት የመራው ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ)፣ ንጉሡን ከሥልጣን ባስወገደ በ 2 ወር ከ 2 ሳምንት ፣ መሪ መፈክሩን መለወጡ የሚታወስ ነው።

https://p.dw.com/p/1DsO6
Äthiopischer Kaiser Haile Selassie zu Besuch in Bonn 1973
ምስል picture alliance/AP/Hinninger

ኅዳር 14 ,1967 ዓ ም፤ 60 የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ፤ የሲቭልና የጦር ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ፤ በአንድ ምሽት ረሸነ። ድርጊቱም፤ በአብዮቱ ሰላማዊ ለውጥ ተካሄዷል ብሎ ሂደቱን ያደንቅ የነበረውን የኢትዮጵያን ሕብረተሰብና የዓለምን ማሕበረሰብ ማስደንገጡ አይዘነጋም። ያ ድርጊት በኢትዮጵያ ታሪክ ያስከተለውን ሁኔታ ከታዘቡት መካከል ፤ በቤልጅግ ኑዋሪ የሆኑትን የፖለቲካና ኤኮኖሚ ምሁር አቶ አበራ የማነ አብንን በስልክ አነጋግረናል።

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ