1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኪንሻሳ ላይ የተሰነዘረዉ ጥቃት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 22 2006

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የፕሬዚዳንት ካቢላ መንግሥት ላይ ትናንት ማለዳ የተሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት ሙሉ በሙሉ መክሸፉና ጥቃቱን ከሰነዘሩት ክፍሎች ገሚሱ በቁጥጥር ስል መዋሉ ቀሪው መደምሰሱ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1Ajp7
ምስል Reuters

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የፕሬዚዳንት ካቢላ መንግሥት ላይ ትናንት ማለዳ የተሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት ሙሉ በሙሉ መክሸፉና ጥቃቱን ከሰነዘሩት ክፍሎች ገሚሱ በቁጥጥር ስል መዋሉ ቀሪው መደምሰሱ ተነገረ። ጆሴፍ ሙኩንጉቢላ ሙቶምቦ የተባሉት ወንጌል ሰባኪ ታማኝ እንደነበሩ የተነገረላቸው ታጣቂ ወጣቶች ትናንት የሀገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ፣ ዓየር ማረፊያ እና የጦር ዕዝ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ተቆጣጥረው እንደነበር መነገሩ ይታወሳል። የኮንጎ መንግሥት ከኪንሻሳ እና ብራስል ዛሬ እንዳስታወቀው የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ስምንት የመንግስት ወታደሮችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱን ያቀናበሩት ወንጌላዊ በሽሽት ላይ እንደሚገኙም የኮንጎ መንግሥት አክሎ ገልጿል። ይሁንና ወንጌል ሰባኪው ከሀገር ሸሽተዋል በሚል የተሰራጨውን ዘገባ በማስተባበል ፕሬዚዳንት ካቢላ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ